Prof. Donald N. Levineበቅርቡ አሜሪካዊው ፕሮፌሠር ዶናልድ ሌቪን ”ኦባማ እና ኢትዮጵያ - ከተስፋ ማጣት ወደ መሪነት” በሚል በእንግሊዝኛ ያቀረቡትን ጽሑፍ በሀገር ውስጥ የሚታተመው ”እንቢልታ” የተሰኘው ጋዜጣ ወደ አማርኛ ተርጉሞ ለንባብ አብቅቶታል። ይህንኑ ትርጉም የኢትዮጵያ ዛሬ ታዳሚዎች በሀገራቸው ቋንቋ ቢያነቡት ለግንዛቤ ይረዳቸዋል በሚል እንደወረደ አቅርበነዋል።

 

ፕሮፌሠር ዶናልድ በዚህ ጽሑፋቸው ላይ “የኃይል አቅርቦትና አጠቃቀምን ማሣደግ”፣ “የውጭ ፖሊሲን መለወጥ”፣ “የፖለቲካ ኃይልን እንደገና ማዋቀር” እንዲሁም “ጥሪ ለኢትዮጵያውያን” የሚሉ ንዑስ ርዕሶችን አካተዋል። ፕ/ሩ በዚህ ጽሑፋቸው ላይ ለኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።

 

ዶናልድ ሌቪን በቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የሶሊዮሎጂ ፕሮፌሠር ነበሩ። የሴናተር ባራክ ኦባማ የቅርብ ወዳጅ ከመሆናቸው በተጨማሪ ኦባማ በቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ሲያስተምር በነበረበት ጊዜ ባልደረባቸው ነበር። ፕ/ር ሌቪን በኢትዮጵያ ማኅበረሠብ በርካታ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ሲሆን፣ “Wax and Gold” እና ”Greater Ethiopia” የተሠኙ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅተዋል። ለዚህ ሥራቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል። (ሙሉውን ትርጉም በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ