ብዙዎቻችን የነጻው ፕሬስ ኣባላቶች ስራዎቻችንን የምናዘጋጀው ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ነበር። ያን ጊዜ። ኣንድ የጋዜጣ ኣሳታሚና ኣዘጋጅ ከናዝሬት አየተመላለሰ ጋዜጣውን ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ያሳትማል። ይህ ወጣት ጋዜጠኛ ዳንኤል ክፍሌ ይባላል። ጋዜጣውም ''ፈንዲሻ'' ትባል ነበር። 



ፈንዲሻ ''ታምራት ላይኔ በስኩዋር ይታማሉ'' ሲል ዜናውን ለቀቀ። የጋዜጣው ኣሳታሚ ዳንኤል ክፍሌም ማአከላዊ ታሰረ።

ታምራት ላይኔ በቀን አስከ ፫ ግዜ ስልክ ወደ ማአከላዊ ይደውሉ ነበር። ዳንኤልን ለማስቀጥቀጥ ብቻ። ዳንኤል ክፍሌን ማአከላው አስር ቤት፣ በአስር ቤቱ ጣራ ላይ አንዲያድር ኣድርገዋል። በወቅቱ ዳንኤል ''ብርድ ገደለኝ... ኣውርዱኝና አስር ቤቱ ውስጥ በስነ ስርዓት አስሩኝ'' በማለት ላቀረበው የስቃይ ኣቤቱታ ''ኣንተ በጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ላይ ከጻፍክ ጀምሮ ሰውየው ምግብም ኣልተመገቡም ደውለው ነግረውናል በደንብ አንድናሽህ '' ነበር የማአከላዊ አስር ቤት ሃላፊዎች መልስ። 

የፈንዲሻው ዳንኤል ክፍሌ ይህን ሁሉ ፍዳ ኣይቶ፣ ከተወሰነ ጊዜ በሁዋላ በዋስ ተለቆና የተንጠለጠለ ክሱን ሳይጨርስ፣

''...ስኩዋር ኣትብላ ተብዬ ስመከር፣ ስመከር፣ ስመከር'' የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔን ድምጽ በቴሌቪዥን ሰማም፣ ኣየም። ''ኣትፍረድ ይፍረድብሃል'' አንዲሉ።

ታምራት ላይኔ አስር ቤት አስከተወረወሩበት ጊዜ ድረስ በጨካኝነታቸው የምናውቃቸው ብዙዎች ነን።በኢትዮጵያ ላይ ካደረሱት በተለየ ለነጻው ፕሬስ መዥገር ነበሩ።

ኣቶ ታምራት ላይኔ የቃለ ምልልሳቸውን መግቢያ ''... ስበድልህ፣ ሳሽህ፣ ስገድልህ፣ የነበረ ህዝብ ...በቅድሚያ ይቅር በሚለው አግዚኣብሄር ስም አናንተም ይቅር ትሉኝ ዘንድ ''ብለው ቢሆን ኖሮ አኔም ''ፈንዲሻንና'' ዳንኤልን ኣላስታውስም ነበር። 
(ሙሉ ቃለ ምልልሱን ለማዳመጥ ይህንን ይጫኑ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ