አቤቶኪቻው

ኮሎኔል ሃይማኖት የአቶገብረዋህድ ባለቤት ናቸው፡፡ ከጫካ ታግለው መጥተው ሹመት በሹመት ሆነውሲሾም ያልበላ ሲሻር ምን ሊበላ ነውብለው ሲበሉ፣ ሲበሉ፣ ሲበሉ… ”የተበሉሴትዮ ናቸው፡፡

 

አቶ ገብረውሃድ ማለት ደግሞ፤ስልጣናቸውን በመጠቀም ያከማቹት መሬት ቢሰበሰብ ኤርትራን የሚያክል ሀገር ይወጣዋል እና ትልቁ ስጋት ሰውዬው መሬቱን ለምን ወሰዱሳይሆን ይሄንን መሬት ይዤ የራሴን እድል በራሴ ወስኛለሁ እና የመገንጠል መብቴ ይከበርልኝ እንዳይሉ ነው…” በሚል ሀገሬው ሲያማቸው የነበሩ ግለሰብ ናቸው፡፡

 

እንግዲህ እኒህ ቱባ ባለስልጣን ቱባ ቱባ ዝርፊያ አድርገዋል ተብለው ሲታሰሩ ባለቤታቸው ኮሌኔል ሃይማኖት ደግሞ የራሳቸውንም የባለቤታቸውም ዝርፊያ ውጤት የሆነውን ንብረትለማንኛውም መደበቅ ነው የሚሻለው…” ብለው ሲያሸሹ ተገኝተው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

 

ከላይ ያየነው ከመንግስት ሚዲያዎች እንደሰማነው እና በራሳችን ቋንቋ ተርጉምን እንደፃፍነው ነው፡፡

 

ይሄን ያክል ከተንደረደርን፤

 

ኮሎኔል ሃይማኖት አዲሱን አመት በእስር ቤታቸው ድል ያለ ድግስ ደግሰው ቤተሰቦቻቸው እዛው ቃሊቲ ድረስ ሄደውላቸው ያማራቸውን ለብሰው ያሰኛቸውን በልተው ደስ ያላቸውን ጠጥተው ስቀው ተጫውተው ነው ያሳለፉት፡፡

 

ከሁለት ቀን በፊት ከጋዜጠኛ ርዮት አለሙ ጋር ክፍል የተጋሩት ኮሎኔል ከጋዜጠኛይቱ ጋር ከተገናኙበት ቀን አንስቶቀልባቸው አልወደዳትምይዝቱባታል፡፡ ይሰድቧታል፡፡ ያንጓጥጧታል፡፡ ለዚህ ደግሞ የስጋ ዘመዳቸው ሆነቸው የቃሊቲ ሴትዋርዲያዎች ሃላፊ አሚናዘርእሰይ አበጀሽ የኛ ልጅብላላቸዋለች፡፡

 

ሙስና ይብቃብላ ስትፅፍ ተገኝታ በቁጥጥር ስር የዋለችው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ፤ ከእናት እና ከአባቷ ውጪ ሌላ ሰው ማናገር አትችይም ተብላ ስትከለከል፤ ሙስና ይስፋ ብለው በሙስና የተዘረፈ ንብረቶችን ሲያሸሹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኮሎኔል ያለ የሌለ ሃይላቸውን ተጠቅመው ሊያበሳጯት እየተጉ ነው፡፡ ለዚህም አበል እንዲሆን በዓልን እስር ቤቱ መኖሪያ ቤታቸው እስኪ መስል ድረስ አሸብርቀውበት ውለዋል፡፡

 

በተቃራኒው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በዓሉን በርሃብ አድማ አሳልፋለች፡፡ እንደ ኮለኔሏ እና እንደዋርዲያዎቹ ዛቻ ከሆነ ርዮትአለሙን በተለያየ ዘዴ ምግብ መመረዝን ጨምሮ ጥቃት ሊያደርሱባት እንደሚችሉዝተውባታል፡፡

 

ኮሎኖል ሃይማኖትን ያሰራቸው አካል በጥፋታቸው እስር አስሯቸው ይሁን በስልጣናቸው ስራ እያሰራቸው ይሁን ግራ ተጋብተን እንገኛለን! ማሰሩ ከሆነግን፤ ይሄ እስር ሙስናን የሚዋጋ ሳይሆን ጭራሽ በሙስና የሚያስወጋ ነውና እና ዛሬውኑ ይፈቱልን! ጋዜጠኛ ርዮት አለሙም ትፈታልን! ሌላው ይቅርቢያንስ እስር ቤት ውስጥ ድጋሚ መታሰሯ ይቁም!

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ