ተመስገን ደሳለኝ

(እለተ እሁድ በ22/04/04 የምሁራኑ ፊት-አውራሪ (የሚያምኑበትን በማንፀባረቅ)፤ እንዲሁም የ‹‹መባል ያለበት መባል አለበት›› ፍልስፍና ተከታይ የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በመኢአድ ቢሮ ተገኝተው ‹‹ህጋዊ አስተዳደር እና የመብት ጥያቄ›› በሚል ርዕስ ስር አንድ ጽሁፍ አቀረቡ። ፅሁፋቸውንም ሀሳብ ወደ መሬት አውርደው ለአድማጭ በሚገባ መልክ ተነተኑ። በትንታኔአቸውም የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ ፀሐፊ ከነበሩት አለቃ ዘነበ እንዲህ የሚል ቃል መዋሳቸውን ነገሩን። ‹‹…ሀገር በእጃችን…።›› አፄው የዘመነ መሳፍንትን የስልጣን መተራመስ ተሻግረው ማእከላዊ መንግስትን ለመመስረት ሲጣደፉ የስልጣን ጠቅላይነታቸውን ‹‹ሀገር በእጃችን›› ሲሉ ፍካሬያዊ ትርጓሜ ሰጡት። እነሆ አለቃንም ዶ/ሩንም ደርቤ አመስግኜ ቃሉን ለዚህ ፅሁፍ ርእስ ይሆነኝ ዘንድ ተዋስኩ)

 

ለመሆኑ ‹‹ሀገር በእጃችን…›› ማለት ምን ማለት ይሆን? … 80 ብሔር ብሔረሰቦችን፣ 80ሚሊዮን ህዝቦችን፣ ራስ ዳሽን ተራራን፣ የጢያ ትክልን፣ የአዋሽ ወንዝን፣ ምናምንን ከእነግሳንግሱ ጠቅልለን እንደ እህል በጆንያ እንሸከመዋለን ማለት ይሆን? ግን እኮ ኢህአዴግ እንዲህ ቢል አይደንቅም። ከእውነታው ብዙም አልራቀምና። ለነገሩ አሁንስ አልጠቀለለንም እንዴ? ልክ በንጉሳዊያን እና በዘመነ መሳፍንት ጊዜ እንደነበረው አባትየው ሲሞት፣ የበኩር ልጁ ተተክቶ ‹‹የሞትንም እኛ፤ ያለንም እኛ›› ብሎ ስልጣን እንደሚይዘው ነው ‹‹ነገረ-ኢህአዴግ››ም።


እናም አውራው ፓርቲያችን ከተማ የሚያህል መንደር በ‹‹ልማት›› ስም አፍርሶ ሲያበቃ ‹‹ለምን አብራችሁኝ እስክስታ አልወረዳችሁም?›› ሲል ያፈጣል። እንኳን አርሶ እና ዘርቶ ቀርቶ፣ ገበሬም ሆኖ የማያውቀውን መንገደኛ ‹‹ኢንቨስተር ገበሬ›› ብሎ መሸለሙን ወንዶች በጭብጨባ፤ ሴቶች በእልልታ ያመስግኑልኝ ይላል። ራሱ ሽብር በሽብር የሆነ፣ የአሸባሪ ህግም ካፀደቀ በኋላ ያሻውን፣ አሸባሪ፣ ያሻውን የአኬልዳማ ተዋናይ ማድረጉንም የአስተዳደር ዘይቤ ነው ይልሃል። የመንግስትንም ሆነ የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኛንም ‹‹ስዘፍን ካልተቀበለኝ፤ ጋጠ-ወጥ ነው›› ይልና ይዘልፋል… ኢህአዴግ እንዲህ ነው። ሀገር በእጃችንም ማለት ይኸው ነው ሌላ አይደለም።


እዚህች ጋር አንድ መታወስ ያለበት ታሪክ አለ፡፡ የታሪኩ መቼት የአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ነው። ታሪኩ ደግሞ በወቅቱ የነበረ የአንድ አዝማሪ ነው። አዎ! አዝማሪው የጊዜውን ፖለቲካ ምርጥ በሆነ ግጥም ነበር የገለፀው። ይሄ ግጥምም ዛሬም ድረስ እንደ ማብራሪያ በመጥቀሙ ነው ታሪክ ሊሆን የቻለው። ያ አዝማሪ ያዘመረው ፖለቲካም እንዲህ ይላል፡-
‹‹ከላይ ሰውየው ከታች ገብርየው

መሀሉን ንሻ ዝምብየው››


ኦኦኦ…ግሩም ድንቅ ፖለቲካ። ከላይ አፄ ቴውድሮስ፣ ከስር ፊት-አውራሪ ገብርዬ። መሀሉን ተራው ኢትዮጵዊ። ዛሬም ያለው ይሄው ነው፤ ከላይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ፣ ከታች ከጄነራል ሳሞራ፤ መሀሉን ደግሞ እኔና አንተ ሆነን፤ እንደ ገና ዳቦ… ማለት ነው፡፡

አዝማሪው ካልተዋጠልህም በፖለቲካ ተንታኞች አስተንትነው፤ መደምደሚያው ይኼው ሆኖ ታገኘዋለህ። የአፄ ኃ/ስላሴ ፊውዳሊዝም ወይም የመንግስቱ ሀይለማርያም ሁሉን በአንድ አካቶ የመግዛት (ቶታሊተሪያን) አሊያም የመለስ ዜናዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲ። ሶስቱም በአካል የተለያዩ ሲሆኑ በተግባር አንድ ናቸው። ‹‹ሀገር በእጃችን›› ናቸውና።

በእርግጥ መንግስቱ ኃ/ማርያም እና መለስ ዜናዊ ‹‹ጠፊ እና አጥፊ›› ሆነው ለ17 አመታት የተፋለሙ ቢሆኑም ብዙ ተመሳሳይ ነገር አላቸው። ለምሳሌ መንግስቱ ኃ/ማርያም ለሚወስዳቸው ህገ ወጥ እርምጃዎች ሲሰሙት የሚጥም ምክንያት ነበረው። ‹‹ለአብዮታዊ እናት ሀገር...›› የሚባል። በዚህ መለስ ዜናዊም አቻ ናቸው። ‹‹አቢዮታዊ ዴሞክራሲ›› እና ‹‹ልማት…›› የሚሉት ‹‹መኮነኛ›› እና ‹‹ማፅደቂያ›› መጽሐፍ ቅዱስ አላቸውና። ይሄ መጻሀፋቸው ወንጌል ብቻ ሳይሆን፣ ትንቢትም አለው። ያውም እንዲህ የሚል ‹‹ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ውጪ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ እንደ ዩጎዝላቪያ መሆኑ ነው›› (መሰረታዊ ጥያቄዎች በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ኢህአድግ ያዘጋጀው መጸሀፍ እንደገለጸው) መቼም ሶስት ሺ አመት እንደ ዩጎዝላቪያ ሳንበታተን የኖርነው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማእቀፍ ውስጥ ሆነን አይመስለኝም።

ሁለቱም ‹‹የፓርቲ አባል›› የማብዛት ሱስ አለባቸው። መንጌ ሳር ቅጠሉ የኢሰፓ አባል ይሆን ዘንድ እንደተጋው፤ መለስም እንኳን ኢትዮጵያውያን ቀርቶ በአዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶችም የኢህአዴግ አባል ይሆኑላቸው ዘንድ ከአቡነ ጳውሎስ ጋር ይፀልያሉ። በእርግጥ የአቡኑን መስቀል ሲሳለሙ እንጂ፤ ሲፀልዩ አላየሁም። ያው ከተሳለሙ መፀለያቸው አይቀርም ብዬ ነው።

ሁለቱም ‹‹መንግስቱ ይውረድ››ም ሆነ ‹‹መለስ ይውረድ›› የሚሉ ተቃውሞዎችን ‹‹ኢትዮጵያ ትውደም›› ሲሉ ይተረጉሙታል። ሁለቱም ራሳቸው ያወጡትን ህግ፣ ራሳቸው ይከሱበታል፣ ራሳቸው ይዳኙበታል፣ ራሳቸው ይፈርዱበታል፣ ራሳቸው ምህረት ይሰጡበታል… ይሄንንም ‹‹የህግ የበላይነት›› ይሉታል። … ድንቄም የህግ የበላይነት። ይህንን ሁኔታ በግልጽ ‹‹ሀገር በእጃችን›› ቢሉት ቢያንስ ‹‹ውሸታም›› ከመባል ይድኑ ነበር።


የሆነ ሆኖ ኢህአዴግ ‹‹ሀገር በእጃችን›› ካለን ከርሟል። የተመሰረተውም በ‹‹አምባገነናዊ አስተዳደር›› ላይ ነው። በእርግጥ አስተዳደሩን ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› እናድርገው ቢሉ ጠቅላላው መዋቅራቸው ይናጋል። ለምሳሌ ኃ/ስላሴ ‹‹የመሬት ላራሹን›› ጥያቄ ቢመልሱ ኖሮ፣ ስርዓታቸው ‹‹ባላባታዊ›› (በመሬት ባለቤትነት) በመሆኑ ስልጣናቸውን ያጡ ነበር። መንግስቱ ኃ/ማሪያምም ‹‹ወታደራዊ አገዛዝ አንፈልግም፤ አሁኑኑ ህዝባዊ መንግስት›› የሚለውን የአሲምባ መፈክር ቢቀበል ኖሮ፣ እንኳን 17 አመት፤ 17 ቀንም አይቆይም ነበር። ኢህአዴግም እንዲህ ነው። ነፃ ምርጫ፣ ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ፣ ነፃ የሙያ ማህበራት፣ ገለልተኛ ፍርድ ቤት፣ ገለልተኛ ወታደር… ጂኒ ቁልቋል የሚሉ ነገሮችን ቢሰማ ኖሮ ‹‹ጨዋታው ፈረሰ፣ ዳቦ ተቆረሰ›› ከተባለ አመታት ያልፉ ነበር። እንግዲህ ወደድክም ጠላህም ይሄ የስልጣን መሰረቱ የተጣለበት መንፈስ ነው። መንፈሱ ከሌለ እነሱም የሉም። ለነገሩ አምባገነንነት ባህሪያቸው የመውጣት ፍላጎት ቢኖራቸው ኖሮ፤ ስለ40 ቀን ተዝካር ማክበር እንጂ፣ ስለ40 አመት በስልጣን መቆየት አይነግሩህም ነበር። ነበር ነው ያልኩህ…


....በረከት ስምኦን መጽሐፋቸውን ባስመረቁ ማግስት ከ‹‹ቁም ነገር›› መጽሔት ጋር ባደረጉት ልዩ ቃለ መጠይቅ ላይ ‹‹በኢትዮጵያ ሁኔታ ግን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ብቻ ነው ልማት ሊመጣ የሚችለው›› ቢሉም፤ አለቃቸው መለስ ዜናዊ ለአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማማቶ ተናግረውት በዊክሊክስ በኩል ይፋ በሆነው ምስጢር ‹‹የእድገት መሰረቱ መልካም አመራርና ዴሞክራሲ ነው የሚለውን ሀሳባቸውን (የኦባማን አስተዳድር ማለታቸው ነው) ግን አልቀበለውም። እንዲያውም ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ለእድገት አስፈላጊ ወይም በቂ ስለመሆኑ በታሪክ አንድም አስረጅ የለም›› ማለታቸው የበረከትን አነጋገር በግልጽ ያፈርሰዋል። ለዚህም ነው የሚመሩህ ተወያይተው፣ ተስማምተው እና በባለሙያ አስጠንተው ባፀደቁት እቅድ ሳይሆን በአምባገነንነት (በዘፈቀደ) ነው የሚል ወቃሽ የበዛባቸው። በእርግጥ መለስ እና በረከት ወይም መለስ እና ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እንዲህ ቦሌ እና ጉለሌ የሆነ መግለጫ ቢሰጡም ‹‹ሀገር በእጃቸው›› በመሆኑ ለምን? የሚል ጠያቂ የለባቸውም። ወይም በደህና ጊዜ እንዳይኖር አድርገዋል። ለዚህም በዋናነት ከታጣቂዎቹ እና ከአለቆቻቸው ባሻገርም የፖለቲካ እና የማህበራዊ ልሂቃን (Elite) በመሪ ተዋናይነት ተሰልፈዋል።


በፖለቲካ ሳይንስ ምሁራኖች አስተምህሮት Social elite (ማህበራዊ ልሂቃን) የሚባሉት ከአላሙዲን ጀምሮ የሃይማኖት መሪ እና የእድር ዳኞችን ሳይቀር የሚያካትት ነው። እነዚህ ልሂቃኖች በአገኙት ቀዳዳ ሁሉ የስርአቱ ዕድሜ ከማቱሳላም በላይ ይሆን ዘንድ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በዚህም ወንጀል እየሰሩ እንደሆነ የገባቸው አይመስለኝም። ለምሳሌ አላመዲን በሸራተን ሆቴል እንጀራ እና ወጥ ወይም ከሻኪሶ የወርቅ ጉድጓድ ወርቅ እያወጣ መሸጡ ምንም ጎጂ ነገር የለበትም። ጎጂ ነገር የሚኖረው በበረከት መጽሐፍ ምርቃት ላይ በምርጫ 97 የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በቴሌቪዥን ክርክር ላይ መቅረባቸውን ተከትሎ፣ ቅንጅቱ ኢህአዴግን በክርክሩ በመርታቱ አላሙዲን መከፋቱን በግልፅ የተናገረውን ስትሰማ ነው። ‹‹በረከት በሩን በርግዶላቸው… ሲያቀብጠኝ፤ የአረብ ሳት አስገብቼ…›› ሲል እነ በረከት በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሳይሆን በአፈና መንገድ መጓዝ እንዳለባቸው ማሳሰቡ ወይም መምከሩ ከጎጂም በላይ ጎጂ ነው። ለ‹‹ሀገር በእጃችን››ም መፈጠር አንዱ ምክንያት ይሄ ነው።

ዶ/ር ዳኛቸው በመኢአድ ቢሮ ባቀረቡት ፅሁፍ ላይ sir Isaiah Berlin የተባሉ የኦክስፎርድ ፈላስፋን ጥናት ጠቅሰው ስለ Positive freedom (አዎንታዊ ነፃነት) እና Negative freedom (አሉታዊ ነፃነት) አብራርተዋል። እኚህ እ.ኤ.አ ከ1909-1997 የነበሩት በትውልድ አይሁድ በዜግነት እንግሊዛዊ ፈላስፋ “The two concepts of liberty” በ .ል ር .ስባ .ረ .ትጥ .ትስ . positive freedom እ . negative freedom ንእ .ዲ . ሲ . ያ .ራ .ሉ “Negative liberty is the absence of obstacles barriers or constraints. One has negative liberty to the extent that actions are available to one in this negative sense. Positive liberty is the possibility of acting or the fact of acting in such a way as to take control of one’s life and realize one’s fundamental purposes.


While negative liberty is usually attributed to individual agents. Positive liberty is sometimes attributed to collectivities or to individuals considered primarily as members of given collectivities.”


(አ .ታ . ነ .ነ . የ .ባ .ውሀ .ግይ .ን . ስ .ሜ ‹‹ሀገር በእጃችን›› የሚለው አማርኛ ዛሬ የለም። ‹‹ሀገር በእጄ›› በሚለው ተቀይሮአልና። የሁሉ ነገር አድራጊ ፈጣሪ አንድ እሳቸው ናቸው። ለምሳሌ መንግስታቸውን የሚያስተች እና የሚያስነቅፍ ውሳኔ ወይም እቅድ ተተግብሮ ከተገኘ ‹‹ፓርቲው የወሰነው›› እንደሆነ ይነግሩሀል። በተቃራኒው ደግሞ ውሳኔው በብዙ ህዝብ የሚደገፍ ከሆነ ጆሮህ እስኪደነቁር፣ ልብ ቀጥ እስክትል ‹‹አባይን የደፈረ መሪ›› የሚል መፈክር ትሰማለህ። እንዲያገኝ የሚያደርገው የነፃነቱ መገለጫዎች ተከዋኝነት እንዳይኖራቸው በከባድ እንቅፋቶች መሞላታቸው ነው። በግልባጩ ደግሞ አዎንታዊ ነፃነት የሚባለው የአንድን ሰው ህይወት ለመቆጣጠር እና መሰረታዊ ህልሞችን ለማረጋገጥ የሚቻልባቸው እድሎች መኖሩ ነው። ይህም ሆኖ ብዙውን ግዜ አሉታዊ ነፃነቶች ከግለሰብ መብቶች ጋር ሲዛመዱ፣ አዎንታዊ ነፃነቶች በበኩላቸው ከቡድን ተኮር መብቶች ጋር ይጠቀሳሉ)


እናም አዎንታዊ ነፃነት የፈለከውን ሀይማኖት የመከተል፣ በፈለከው ስም መጠራት (በቀጥታ ከፖለቲካ ጋር የማይገናኙ መብቶችን የሚያጠቃልል) ሲሆን፤ በነፃ መደራጀት፣ መቃወም፣ ሀሳብን በነፃነት መግለፅ፣ መተቸት… ወዘተ ደግሞ አሉታዊ ነፃነት ይባላል። አውራውም ለስልጣኑ የማያሰጋውን አዎንታዊ ነፃነትን ፈቅዶ፤ አሉታዊውን በጥብቅ ከልክሏል። ‹‹ሀገር በእጃችን›› ይሉሀልም ሌላ አይደለም፣ ይኸው ነው።


በእርግጥም አሉታዊ ነፃነትን ቢፈቅዱ ኖሮ እንኳን ለነዚህ ዓመታት ያህል ቀርቶ አንድም ቀን ሚኒልክ ቤተ-መንግስት ማደራቸው አጠራጣሪ ነው። በግልባጩ ደግሞ የፕ/ር በርሊንን የአዎንታዊ ነፃነት ሀቲት በኢትዮጵያዊ አምድ ስናብላላው አዎንታዊ ነፃነት (በአደባባይ ራቁት ሆኖ መሄድ፣ በራስ ላይ ቀንድ ሰክቶ፣ ገላ ላይ መሀረም የምታህል ቆዳ አገልድሞ በየጎዳናው መጨፈር፣ አማራ ነኝ፣ ኦሮሞ ነኝ፣ ትግሬ ነኝ ብትል፣ ብትፈልግ ሙስሊም፣ ብትፈልግ ክርስቲያን ብትሆን፣ ወንዶ እና በለጬህን ብትቅም፣ ሲያሻ ማንቼ እና አርሴ እያልክ ብትዘል፣ ከፈልክ ግብረሰዶማዊም ብትሆን…) ለመለስ ስልጣን አያሰጋም። ስለዚህም የሚከታተል ሰላይም ሆነ በዱላ የሚሸከሽክ ፌዴራል ወይም ‹‹አሸባሪ›› ብሎ ፍርድ ቤት የሚያቆም የለም። Negative freedom (አሉታዊ ነፃነት) ግን እንዲህ እንደዋዛ የምታገኘው አይምሰልህ። ሀሳብን በነፃ መግለፅ ህብረተሰብን ያነቃልና ከየትም አታገኘውም። የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግም በዚህ ውስጥ ይካተታል። ይሄ ደግሞ ድንገት የታህሪንን መንፈስ ሊፈጥር ይችላልና የሚሰማህ የለም።


ለዚህም መጠቀሚያ ይሆኑ ዘንድ ልሂቃኑን በአንባሳው ዙሪያ እንዲሰለፍ ተደርጓል። እንደምታውቀው በልሂቃን መደብ የተማረም ያልተማረም ሊካተት ይችላል። ቁም - ነገሩ በማህበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት አለው፤ የለውም? የሚለው ነው፤ ልህቂ ለመባል። እናም የኢኮኖሚው፣ የማህበራዊው፣ የሃይማኖቱ፣ የባለውቃቢው… ልሂቃን ተሰባስቦ መንገድ ጠራጊ ይሆን ዘንድ ይመረጣል። ከተመረጠ በኋላም እንደ አላሙዲን ‹‹ተራራው ዝቅ ይበል፣ ኮረብታው ከፍ ይበል…›› እያለ ይሰብካል። ከልሂቃኑ በኋላም ካድሬው ይከተላል። በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ስም አጥምቆ ደቀ መዝሙር ያደርግህ ዘንድ። አጥምቆህም ሲያበቃ የሸመደደውን የፓርቲውን ርዕዮት አለም ይሰብክሀል። ስለባለ ራዕዩ መሪም ‹‹ቆራጥነት፣ አዋቂነት፣ የዝናብና የፀሀይ ተከራካሪነት…›› ይተርክልሃል። አየህ! ሀገር በእጃችን ሲሆን እንዲህ ነው። ሁሉ በእጃችን፤ ሁሉ…

የሆነ ሆኖ ‹‹ሀገር በእጃችን›› የሚለው አማርኛ ዛሬ የለም። ‹‹ሀገር በእጄ›› በሚለው ተቀይሮአልና። የሁሉ ነገር አድራጊ ፈጣሪ አንድ እሳቸው ናቸው። ለምሳሌ መንግስታቸውን የሚያስተች እና የሚያስነቅፍ ውሳኔ ወይም እቅድ ተተግብሮ ከተገኘ ‹‹ፓርቲው የወሰነው›› እንደሆነ ይነግሩሀል። በተቃራኒው ደግሞ ውሳኔው በብዙ ህዝብ የሚደገፍ ከሆነ ጆሮህ እስኪደነቁር፣ ልብ ቀጥ እስክትል ‹‹አባይን የደፈረ መሪ›› የሚል መፈክር ትሰማለህ።

በእርግጥ የመለስ አስተዳደር የኮሚኒዝም የስጋ ዘመድ መሆኑ ግልፅ ነው። መዋቅሩም ቢሆን ጠቅላላ ጉባኤ፣ ፖሊት ቢሮ፣ ቸርማን (ዋና ፀሀፊ) እያለ ይሄድና ለቸርማኑ የስልጣን መዓት ያሸክማል። በዚህ መንገድም ሌኒን፣ እስታሊን፣ ማኦ፣ ካስትሮ… መዓት ስልጣን ተሸክመው የጎበጡ ናቸው። ወይም ህዝባቸውን ያጎበጡ ናቸው። ነገርየው ለውጥ የለውም። ቢጎብጡም አንተው ላይ ሆነው በመሆናቸው ሸክሙ ላንተ ነው። ቢያጎብጡህም ተጎጂው አንተ ነህ። ግራ የሚገባህ ግን ይህንን ለህይወትህ ጠቃሚ ነገር አስመስለው ‹‹በኮሚኒዝም ጊዜ የለም ትካዜ›› በሚል ሳውንድ ትራክ አጅበው ሲነግሩህ ነው። …‹‹ሀገር በእጃችን፡፡››


እየሰሩ ያለውም ቢሆን አዲስ ታሪክ አይምሰልህ። ያለፈው ዘመን ቅጥያ ነው። ለምሳሌ የኃይለስላሴ ባለቤት እቴጌ (ቀዳማይ እመቤት) የሚል የክብር መገለጫ ማዕረግ ነበራቸው። የመለስ ዜናዊም ባለቤት የክብር ስማቸው ቀዳማይ እመቤት ነው። በኃይለስላሴ ስርዓት ዋነኛ ተጠቃሚው መኳንንቱ ነበር። በመለስ ስርዓትም ተጠቃሚው በዙሪያቸው ያለው አመራር እና ከፍተኛ ካድሬው ነው። መሬቱንም እስኪበቃው የቸበቸበው ጋዜጠኛ እንዳይመስልህ፤ የአመራር አባላት እንጂ። ኃይለስላሴ የ66ቱ አብዮት ባይነሳባቸው ኖሮ ስልጣን አይለቁም ነበር። ቀናቸው ደርሶ ቢሞቱ እንኳን ስልጣኑ ‹‹ለአልጋ ወራሹ›› ነው። መለስም ቢሆኑ ከእነ ጓደኞቻቸው በቻይና ተተኪ አልጋ ወራሾቻቸውን እያስተማሩ እንደሆነ ከዚህ ቀደም ያወራነው ነው…. እናም እመነኝ ቅጥያ እንጂ አዲስ ታሪክ የለም። ለነገሩ የ60 ዓመት አዛውንት ስለ አርባ አመት ‹‹መግዛት›› ከነገረህ፤ አነጋገሩ ሰምና ወርቅ ለመሆኑ ጥርጣሬ አይግባህ። ምክንያቱም እየነገረህ ያለው ስለወራሾቹ እንጂ ስለ እራሱ መቶ አመት መኖር አይደለምና። ማንም ሰው የቱንም ያህል ሀያል ቢሆን መቼ እንደሚሞት ሊያውቅ አይችልም። ለዚህም ነው ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ብሎ ነገር እና ‹‹በህዝብ፣ ለህዝብ፣ የህዝብ መንግስት›› ብሎ ነገር አራምባና ቆቦ የሆኑት።


መቼም ይሁን መቼ፤ የትም ይሁን የት ‹‹አብዮታዊ…›› የሚለው ቃል ስልጣን በያዘው በኩል ከተሰለፈ ያን ጊዜ ጉድ ይፈላል። ለምሳሌ ማኦ ዜዱንግ “Cultural Revolution (የባህል አብዮት)” አለና የቻይናን ነባሩን ባህል ከስሩ መንግሎ ‹‹የሎው ሪቨር (Yellow River)›› ውስጥ ከተተው። ይህንን እርምጃውን የተቃወሙትንም አንድ በአንድ አድኖ ፈጅቷቸዋል። …መለስም ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ሲሉን ዴሞክራሲ ላይ አብዮት አቀጣጥዬ ‹‹አንተ የምትፈልገውን ዲሞክራሲ›› ተከዜ እከተዋለሁ እያሉን ካልሆነ በቀር የአብረሃም ሊንከን በህዝብ፣ ለህዝብ፣ የህዝብ መንግስትን ሊያመጡ አይችሉም። በእርግጥ አብዮት ሁልጊዜም ሊሳካ አይችልም፤ ሊከሽፍ የሚችልበት እድልም ሰፊ ነው። እናም እድለኛ ከሆንክ… ማን ያውቃል?


የሆነ ሆኖ አምባገነን መንግስት እየቆየ ሲሄድ ከመሻሻል ይልቅ እየተበላሸ ነው የሚሄደው። ይበልጥ ሀያል የሆነ ስለሚመስለውም የእውር ድንብር እርምጃዎቹ ይጨምራሉ። በዚህ ላይ ራሱን ‹‹ሁሉን የሚችል፣ ሁሉን የሚያውቅ፣ ሁሉ ቦታ ያለ›› አድርጎ ይቆጥራል። በተግባር ግን ከቤተ መንግስቱ እልፍኝ ውጪ የትም የለ። እናም ሲያሻው ‹‹ኤልሻዳይ››፣ ሲያሻው ‹‹አዶናይ›› ይሆንብሃል። በዚህም ጊዜ መቃወም፣ መተቸት፣ መንቀፍ አንገት ያስቆርጣል። ኒኮሎ ማኪያቬሊ የሚባለው የአምባገነኖች የጡት አባትም እንዲህ ይልሃል ‹‹ስለሉዑላኑ መናገር፣ አንገት ያስቀነጥሳል።›› እኔም እልሀለሁ፣ ዝም በማለት አንገትህን ከቅንጠሳ ብታተርፍም፣ በዝምታህ (በፈሪነትህ) የአገርህ አንገት ይቀነጠሳልና፣ ዝም አትበል!!

ምንጭ ፍትህ ጋዜጣ (አዲስ አበባ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ