“ሌባው” ዳኛ እና አሸባሪው አዋጅ
በ1988 ከርቸሌ እስር ቤት ውስጥ በብዛት ከነበሩ እስረኞች ውስጥ የስልክ ገመድ ቀበኞች ቁጥር ላል አልነበረም፤እነዚህ የስልክ መስመር ቀበኞች ገመዶቹን እየቆራረጡ መዳቡን ለጌጣገጥ ሰሪዎች የሸጡ ገንዘብ ያገኛሉ፤ሲያዙም ጉዳዩ ተራ ሌብነት በመሆኑ በአጭር ግዜ እስራት ሲለቀቁ ሌብነታቸውን ይቀጥላሉ፤ያኔ እንደዛሬው አሸባሪ የሚል ማጣፈጫ ስላልነበር መንግስትንን እና ሕዝብን ማለያየት የሚል አንቀጽ ተከፍቶባቸው መደዳውን የ8 ዓመት እስራት ሲፈረድባቸው ሌብነቱ ጋብ አለ፤ሕጉ አይፈቅድም የሚል ሙግት የሚያነሱ ባለሙያዎች እንደነበሩ አስታውሳለሁ፤በዚህ የተደፋፈሩት የመንግስት ዐቃቤ ሕጎች የመንገድ ላይ የኤሌክትሪክ አምፖል የሰበረን ግለሰብ ከተማን ወደ ገጠር በመለወጥ የሚል ክስ እንደመሰረቱበት ሲነገር ቆይቷል፣ከአዲስ አበባ የመንገድ ላይ መብራቶች አንዱ በመሰበሩ አዲስ አበባ ወደ 1879 ዓ.ም ስትመለስ አይታያችሁም? የስልክ እና የኤሌክትሪክ መስመር መቁረጥ እነሆ ከ 15 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ ሽብር ሆኖ መጣ።
በዚህ ረገድ የሕወሐት/ኢህአዴግን ተልዕኮ በዋናነት በማስፈጸም በግንባር መስመር ላይ የሚገኘው የያኔው “ሌባ ዳኛ”የዛሬው የኮሚንኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዴኤታ ሽመልስ ከማል ነው፤ በ1988 ዓ.ም ሽመልስም ሆኑ ሌሎቹ በአቶ መለስ አንደበት ሌቦች ተብለው የተባረሩት ዳኞች በወቅቱ ወን ላቸው ዲግሪያቸውን በተልዕኮ ግዢ አለማግኘታቸው፣ሕጉን ማወቃቸው እና በሕጉ መመራታቸው ብቻ ነበር፤አቶ ሽመልስ ዛሬ በሚያሳየው ያልተገባ ድርጊት ያኔ ነበረውን ጥንካሬውን
መካድ ተገቢ አይሆንም፤ያም ብቻ ሳይሆን ከዳኝነት ተባሮ የተወሰነ ግዜ በጋዜጠኝነት አገልግሎ የጥብቅና ፍቃድ ካወጣ በሁዋላም ለጋዜጠኞች በነጻ ጥብቅና እስከመቆም ሄዿል፤ዳኛ በነበረበትም ወቅት ጋዜጠኞች ሕዝብን በመንግስት ላይ ማነሳሳት ተብለን ስንከሰስ አቃቤ ህግ ማስረጃ እያለ የሚያቀርበው ጋዜጣውን በመሆኑ ይህማ ማስረጃ እንዴት ይሆናል? ህዝቡ በመንግስት ላይ ስለመነሳሳቱ ማስረጃ አቅርብ እያለ የልዩነት ድምጹን ያስመዘግቡ ነበር፤ሰብሳቢው ዳኛ የሕወሓት ታጋይ ስለነበሩ፣ከዚህም በላይ ሕግ ስላልተማሩ ከግራ ዳኛው ጋር እየሆኑ ጋዜጠኞችን በሰልፍ ወደ ወህኒ ይነዱ ነበር፤እኚህ ሰው የኢሕአዴግ ካድሬዎች የሚሰለጥኑበት ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ከተከፈተ በሁዋላ ሕግ ተምረው ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደርሰዋል፤አቶ ሽመልስ ብዙ እረፍት ወስዶ በአቋራጭ ቀደማቸው እንጂ ፤......የሕወሐት ሹመት የዛፍ ላይ እንቅልፍ ቢሆንም።.
አቶ ሽመልስ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ድንገት ኒሻን የሚባል ጋዜጣ ይዞ ብቅ አለ፤ባልተጠበቀ ሁኔታ በነበሩት ጋዜጦች ላይ ጦርነት ከፈተ፤ኤርትራ መሬቱን እንደያዘች ተደራደሩ፤የጦርነት ነጋሪት መጎሰማችሁን አቁሙ በማለትም በኢሕአዴግ ባለስልጣናትም ላይ ዘመተ፤ጋዜጦቹ ላይ የሰበቀው ጦር አሰርተውት ሂሳብ በከለከሉት የጋዜጣ ባለቤቶች ምሬት ነው ተብሎ ቢታለፍም፣የሕወ ት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት ግን አልታገሱትም፤ከነባልደረቦቹ ሰብስበው አሰሩት፤ከተወሰነ ግዜ በሁዋላ ተለቀቀ፤በጥብቅና ስራውም ቀጠለ.....የሕወ ትን መሰንጠቅ ተከትሎ አቶ ሽመልስ በየት እና እንዴት እንዳለፈ ሳይታወቅ፣የመንግስት ሰራተኛ መሆኑ ሳይሰማ የብሮድካስቲን ኤ ንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆኖ ብቅ አለ። ምርጫ 97ትን ተከትሎ የቅንጅት መሪዎች እና ጋዜጠኞች ሲታሰሩ ሹመት ደርቦ.፣የቀደመውን ሳይለቅ ዋና አቃቤ ሕግ ሆኖ ተከሰተ፤የ ሰት ምስክር ቆጠረ፤እንቶፈንቶ ወረቀት ከመረ፤በግርገግሩ ጉዳት የደረሰባቸው በማለት የጨጉዋራ እና የአባለዘር በሽተኞችን የ ኪም ማስረጃ ጭምር ይዞ ቀረበ፤ለዚህ አሳፋሪ ተግባር ዕፍረት የማያውቁት የሕወሃት/ኢሕአዴግ መሪዎች የሚኒስትር ዴኤታነት ሹመት ሰጡት ሚኒስትር መስሪያቤት ባያዝበትም።
“ነጻው” ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን መርምሮ፣የሐገሪቱን ወን ለኛ መቅጫ ሳይሆን የአቶ መለስን ግንባር አንብቦ የቀረበባቸው ማስረጃ ከጥርጣሬ በላይ ወን ል መፈጸማቸውን ያሳያል ሲል ዕድሜ ልክ ፈረደ፤የሽመልስ እንጂ የዳኞቹ የሚጠበቅ ነበር፤ሁለቱ የሲቪል ሰርቪስ ተመራቂዎች ሲሆኑ፣ አንዱ ደግሞ በመማር ላይ የነበሩ ሕወሃት ነበሩ፤የዳኞቹ ውሳኔ የማይገርመው ሲቪል ሰርቪስ ድንጋይ ማምረቻ እየተባለ ስለሚጠቀስ ብቻ ሳይሆን እዚህ ተቋም የሚገቡት ሁሉ የኢህአዴግ
አባላት ስለሆኑ ከመነሻው ገለልተኛ አይደሉም።
ከዚህ ተቋም የወጡት ተመሳሳይ ችግራቸው ገለልተኛ አለመሆናቸው እና ለስፍራው አለመመጠናቸው ሲሆን፣እንደ ኤክሰፕሽን የሚወሰዱ በጣም የወረዱ እና የወጡ ያጋጥማሉ፤ ማንብበ እና መጻፍ መቻሉ ጭምር የሚያጠራጥር የሲቪል ሰርቪስ ዳኛ ፊት ቀርቤ አውቃለሁ፤በሌላ በኩል ደግሞ የቅንጅት መሪዎችን የፍርድ ሂደት በሰብሳቢነት የመራው አዲል አሕመድ የተፈጥሮ ንቁነቱ አግዞት ሲቪል ሰርቪስ ተምሮ ጥሩ የሕግ ዕውቀት ወይንም ግንዛቤ እንዳለው አሳይቷል፤ውሳኔው እና የህግ ትንተናው ሕግ በማያውቁ እና ለሕግም ደንታ በሌላቸው የሕወሐት ፖሊት ቢሮ አባላት ተሰርቶ የመጣ መሰለ እንጂ።በ30 ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወጣት በእንደዚህ ያለ አሳፋሪ የፍርድ ውሳኔ ላይ በሰብሳቢ ዳኛነት ፊርማውን ማሳረፉ ሕሊናው ቦታው ሲመለስ ሲያሸማቅቅ የሚኖር ነው።..
ሰሞኑን ጋዜጠኞቹን ውብሸት ታዬን እና ርዕዮት አለሙን አሸባሪ በሚል መግለጫ የሰጠው ሽመልስ ከማል በዚያ የቅንጅት መሪዎች ችሎት በሞት እንዲቀጡ ከጠየቀባቸው ተከሳሾች ውስጥ ጥቂት ከማይባሉት ጋር ይተዋወቃል፤ በተለይ ከሁለቱ ጋር የነበረውን ቅርበት ለሚያውቅ እና በሞት ይቀጡልኝ ብሎ ያደረገውን ሙግት እና እልህ ላየ ሰዎቹ ምን አስነክተውታል የሚያሰኝ ነበር፤በሞት እንዲቀጣ የጠየቀበት የትናንት ገዋደኛው ዳንኤል በቀለ እሱ የማሰለትን መቃብር ፈንቅሎ ዛሬ የአንድ ታዋቂ አለም አቀፍ ድርጅት የአፍሪካ ክፍለ አሕጉር ሃላፊ ሆኗል፤አቶ ሽመልስ ግን ከሕወሐት ተጠግቶ ጥላቻቸውን ለብሶ ልብወለድ ወን ል እየፈጠረ፣ፎር ሪ ማስረጃ እያቀናበረ የሞት አንቀጽ እየጠቀሰ የነፍሰ ገዳዮቹ ማህበር ቋሚ ተሰላፊ በመሆን እስከውድቀታቸው ለማገልገልየቆረበ መስሏል።ሽመልስ .እንዲህ ሳይለይለት፣የአቶ በረከት ጥላቻ በልኩ ሳይሰፋለት በፊት የብሮድካስቲነግ ኤ ንሲ ስራ አስኪያጅ በነበረበት ወቅት ስልክ ደውሎ የተናገረኝ በአዳዲስ ፈጠራ ወደ አደባባይ በመጣ ቁጥር ትዝ ይለኛል፤ በ‘ኢትኦጵ’ ጋዜጣ ላይ ስለህወ ት በተጻፈ ጽሁፍ ውስጥ የርሱም ስም አብሮ ይነሳል፤በአንድ ወገኑ ቤተሰቦቹ የኤርትራ ተወላጆች ስለመሆናቸው ጽሁፉ ይጠቅሳል፤ይህንን አይቶ ነበር አቶ ሽመልስ ስልክ የደወለለልኝ፤ማንነቱን ሳይነግረኝ ማንነቴን ሳያረጋግጥ እኔ ኤርትራዊ ለመሆኔ ማስረጃህ ምንድን ነው ? ሲል ጠየቀኝ፤አልተግባባንም፤ “እኔ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ አይደለሁም ኣሳታሚነቱንም በፍርድ ቤት ውክልና ለሌላ ሰው አስተላልፌያለሁ፤አዘጋጆቹጋ ደውል” አልኩት፤ “እሱን ሂድና ለማያውቅ ሰው ተናገር፤ደሞ አዘጋጁ ሌላ ሰው ነው ብለህ ለኔ ስትናገር አታፍርም ወይ?” ሲል ትንሽ ተጨቃጨቅን።
ከኤርትራዊ ቤተሰቦች ተወለደ ማለት ወን ል ነው እንዴ?”በማለት ስጠይቀወ “ ሲሳይ በጣም አዝናለሁ፤ዛሬ የነዚያ ዘረኞች መሳሪያ በመሆንህ” ሲል ወቀሰኝ፤ እነዚያ ዘረኞች ያለው ከሕወሐት ተነጥሎ የወጣውን የአቶ ተወልደ/ስየን ቡድን ነው፤ሽመልስን ወደዚህ የገፋው በእኛ ጋዜጣ ላይ “ከሕወሐት መንደር” በሚለው ገጽ በሕወሐት ዙሪያ ተከታታይ ሪፖርት የሚጽፉት የተባረሩት የህወሃት ሰዎች ናቸው ብሎ በማመኑ ነበር፤እኔም በስልክ በሰጠሁት አጸፋ “በይፋ ተሹመህ የዘረኞች መሳሪያ የሆንከው አንተ ነህ” ስለው በሙያዬ ነው የማገለግለው የሚል አላስፈላጊ ሙግት ሊገጥመኝ ሞከረ፤ከዚያም ስልኩ ይቋረጥ ይዝጋብኝ አለየሁም፤ ብቻ በዚሁ ተለያየን።
አዲስ እና አፋኝ የፕሬስ ሕግ ለማስጸደቅ በተጠራ ስብሰባ ላይ ከወራት በሗላ አስረጂ ሆኖ መጣ፤ሕጉ ከውስጥም ከውጭም በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ተንጠልጥሎ ባለበት አንዳንድ አንቀጾች ተቆርጠው ወን ለኛ መቅጫ ውስጥ እንዲገቡና እንዲጸድቁ ተደረገ፤ከገቡት አንቀጾች አንዱ ዋና አዘጋጁ የይስሙላ ከሆነ የጋዜጣው ባለቤት ወይንም አሳታሚው ይጠየቃል የሚል ነው፤ዋና አዘጋጁን አነጋግረው ስለው ሽመልስ ያለው ትዝ አላችሁ? ውብሸት እና ርዕዮትን አሸባሪዎች እንደሆኑ በአደባባይ የተናገረው ሰው የሕይወት ታሪክ ከ1988 እስከአሁን በአጭሩ ይህን ይመስላል፤ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት አለሙ በአሸባሪው አዋጅ ወደ ወህኒ ሲጋዙ፤የታሰሩት በጻፉት አይደለም እያሉ እየነገሩን፣ከቤታቸው በርብረው የወሰዱት ግን ጋዜጣ እና ሲዲዎችን እንጂ የጦር መሳሪያ አለመሆኑ ልብ ይሉዋል።ለጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ለመምህርት ርዕዮት አለሙ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት እና የሰብኣዊ መብት ድርጅቶች የሰጡት አፋጣኝ ምላሽ የሚያስደስት ሲሆን፣በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ለእነዚህና ለሌሎቹ ታሳሪዎች ድምጻቸን ማሰማት ይገባቸዋል።
እነዚህ ታሳሪ ኢትዮጵያውያን ወን ል እንዳልፈጸሙ የማምነው በዚህ መንግስት የቀደመ የጎደፈ ታሪክ በመነሳት ብቻ ሳይሆን፣ወን ለኛን የመከታተል እና የመመርመር አቅማቸው ደካማ መሆኑን ጭምር ስለምረዳ ነው፤በኢትዮጵያ ያሉ የፖሊስ ባለሙያዎች ትከሻቸው ላይ የደረደሩትን ማዕረግ እንዴት እንዳገኙት ገር ቤት ያለው ኢትዮጵያዊ በሚገባ ያስታውሰዋል፤ፖሊስ ገለልተኛ ነው የሚባለው ወረቀት ላይ ብቻ በመሆኑ ታማኞች ተመርጠው አንዳንዶች አንድ ሳምንት ፣ሌሎች ሁለት ሳምንት ሰንዳፋ ፖሊስ ኮሌጅ ቆይተው ንፋስ ወስደው ሲመለሱ ትልልቁን ማዕረግ ለበሱ፤ይህን ሻሞ ሹመት ከማንም በፊት የሰሙትና የተገረሙት ራሳቸው ፖሊሶቹ ስለነበሩ ማዕረግ አሰጣጡን ላቭሊ ሲሉ ገለጹት፤ላቭሊ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በማስታወቂያው የሚታወቅ እና ገር ቤት የሚመረት ብስኩት ነው፤ማስታወቂየው በስኩቱ ትኩስ መሆኑን ለማመልከት “ጠዋት ተመርቶ፣ ከሰዓት መርካቶ”ይላል።...
አሶሳ ላይ ከወደቀ የኤሌክትሪክ ምሶሶ ጋር እነዚህን ጸሃፊዎች ማገናኘት የጻፉት ጋዜጣ ላይ የፖሎቹ አጣጣል መርሃ ግብር ካልሰፈረ ወይንም በኮድ ካልተቀመረ በቀር ከሳሾቹ ረሳቸውን እንጂ ማንንም ማሳመን አይችሉም፤የኢሕአዴግ የስለላ እና የፖሊስ መዋቅር ችግር በመስኩ ላይ የበሰሉ ባለሙያዎችን ባለመያዙ አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር “የዓይኑ ቀለም’ ያላማረውን ሁሉ ያስራል፤ካሰረ በሁዋላ ማስረጃ ይፈበርካል፤የሚፈበረኩት ማስረጃዎች ደግሞ ምን ያህል የልጅ ስራዎች እንደሆኑ አይተናል፤የሚያሳፍሩ ብቻ ሳይሆን የሚያሸማቅቁ ፎር ሪዎች ታዝበናል፤የጸረ ሽብር አዋጅ በማለት በሚያንቆለጳጵሱት እና በተግባር ዋና አሸባሪ ሆኖ በተቀመጠው አዋጅ የተከሰሰ ሰው በመደበኛ የክስ ሂደት የሚከለከሉ የሰሚሰሚ ማስረጃዎች እንዲቀርቡበት የተፈቀዱ በመሆኑ፣እንዲሁም ራሳቸው ለማስረጃ ብለው የቀረጹዋቸውን የስልክ ውይይቶች በድምጽ ሶፍትዌሮች እያቀጠኑና እያወፈሩ እንደትልቅ ግኝት ሊያቀርቡም ይችሉ ይሆናል፤ዱባይ ድረስ ተከታትለን ያዝናቸው ብለው በጄኔራሎቹ ዙሪያ ያቀናበሩትን የሕጻን ስራ ለሚያስታውስ ስራቸው ሁሉ የደመነፍስ እና የጨበጣ መሆኑ ይከሰትለታል፤...በግ ይዞ ውሻ መሆኗን አምናለች አይነት ማስረጃ በሚቀርብበት፣በግ እንዴት ውሻ ሊሆን ይችላል የሚል ፍርድ ቤት በሌለበት እስሩም ሁሉም ይቀጥላል፤ጥር ላይ ሆነው የዋጋ ተመን ሲያወጡ የካቲት ምን ሊከሰት እንደሚችል መተንበይ በማይችሉት “ሊቁ መሪያችን” ችግር እና ስቃይ ሊቀ ሊቃውነት ሆኖ እንደነገሰብን ያበቃልናል፤በጋራ መቆም እስካልቻልን ድረስ።....
ሁለቱ ጸሃፊዎች የሚሰሩባቸው አውራምባ ታይምስ እና ፍትህ ጋዜጣ “እንደንጉሱ አጎንብሱ” ከሚለው ከምርጫ 97 ወዲህ ከመጣው ያልተጻፈ መመሪያ ትንሽ እያለፉ፣ቀዩን መስመር እደፈሩ በመሆናቸው ለእነሱም፣ለሌላውም ትምህርት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ለጸረ ሽብር ሕጉ ማብሰሪያ ይሆን ጭምር ርምጃው እንደተወሰደ መገመት ይቻላል፤ለምን ዋና አዘጋጆቹን አልተያዙም ለሚሉ ዋና አዘጋጆች ከታሰሩ ጉዳዩ ቀጥታ ከሚዲያ ጋር የተያያዘ ስለሚመስል “የኒዮ ሊበራሎች” ጫጫታ ይበዛል በሚል ጩሓት መቀነሻ ተብሎ እንደተወሰደ መጠራጠር ይቻላል፤ምን ያህል የግሉን ሚዲያ ሽባ እንዳደረጉት እና ከሕግ ውጭ በስልክ ተግሳጽ በተሰመረው መስመር እንዲጉዋዙ እንደሚያደርጉ በ1999 መጨረሻ በአንድ ጋዜጣ ላይ የታየውን መጥቀስ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ሊከበር የቀረው ከሁለት ወራት ያነሰ ግዜ ነበር፤ለሚሊኒየሙ በአለም ዙሪያ የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ነቅሎ በኢትዮጵያ እንደሚገኝ ተደጋግሞ ስለተነገረ ቤት አከራዮች በተከራዮቻቸው ላይ ኪራይ በመጨመር እያስለቀቁ ለዲያስፖራው በዶላር ለማከራየት ሲዘጋጁ፣ገንዘብ ያላቸው መኪኖችን በብዛት ገዝተው በኪራይ ለመክበር ተጣድፈዋል፤ሶስት እና አራት ወራት ሲቀረው ይገባል የተባለው ዲያስፖራ ሳምንታት እስከቀሩበት ነ ሴ አጋማሽ ድረስ የውሃ ሽታ ሆነ፤ይሄኔ ነበር አከራዮች መቆጨት፣ባለመኪኖቹ በኪሳራቸው መብገን የ መሩት፤ይህንን ሰው ውስጥ ያለውን ስሜት ይዞ አንዱ ጋዜጣ ሚሊኒየሙ ደረሰ፣ሆቴልም አልተጨናናቀም፤ዲያስፖራውም አልታየም(ቃል በቃል ላስታውሰው አልቻልኩም) የሚል ዘገባ አቀረበ፤ጋዜጣው ከወጣ በሗላ ከአቶ በረከት ቢሮ ምን እየሰራችሁ ነው? የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ሲመጣ፤ጋዜጣው በሳምንቱ ሚሊኒየሙ ሞቅሞቅ እያለ ነው የሚል ዘገባ በማቅረብ ዕውነቱን ሳይሆን፣እነ አቶ በረከት የሚመኙትን ጽፎ
ተገላግሏል፤ተግሳጽ አልሰማ ያሉ የአሸባሪነት ማዕረግ ተሰጥቷቸው ወደ ወህኒ ተግዘዋል፤አቶ በረከት ቢሮ እና ፌደራል ፖሊስ ቢሮ እየተጠሩ የተመከሩ ብዙዎች ቢሆኑም፣ምክር አልሰማ ያሉት ጋዜጣቸውን ዘግተው ሲሰደዱ፣እነሆ ቀሪዎቹም አሸባሪ ተባሉ።...
እነ አቶ በረከት ሁሉንም ሰው ደራሲ ተስፋዬ ገብርአብ በጋዜጠኛው ማስታወሻ ላይ እንዳስቀመጣቸው ጄኔራል ማለትም በአቶ በረከት ቃለ ምልልስ ስማቸው እና ምስላቸው እንደወጣው ያስባሉ፤ለቪኦኤ ባለስልጣናት እነ ዕከሌን በጣቢያችሁ አታቅርቡ የሚል መሳሰቢያ ይሁን ልመና ሲያቀርቡ ራሳቸው አቶ በረከትን በጄነራሉ ቦታ አገኘሗዋቸው፡፤ ስለ አሜሪካ ሚዲያ ወይንም በዚያች ምድር ስላላ ነጻነት ለማወቅ የአሜሪካን ሕገ መንግስት ማንበብ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፤ የአሜሪካንን ነጻነት እንኩዋን አቶ በረከት ቢሮ የሄዱት የቪኦኤ ልኡካን ኮንግረሱም፣ሴኔቱም፣ኦባማም ማንም ሊገሰው አይችሉም፤በሕገ መንግስታቸው ያስቀመጡትን ነጸነት ለማስፋት እና ለማብራራት እንደ ምሶሶ የሚወሰድ ማጠናከሪያ በማስገባት ለነጻነት ይበልጥ ዋሰትና የሚሰጡትን አሜሪካውያንን በሰሜን ኮርያ ሂሳብ ማነጋገር የጤና አይመስለኝም፤ቪኦኤ ዘገባውን ከአርካይቭ ውስጥ ማውጣቱም ሆነ የልዕኩ መሪ ዴቪድ አርኖልድ መታገዳቸው ይህንን ዕውነታ አይለውጠውም።
እነሆ አድራሻዬ፦ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
01 ሐምሌ 2003



