የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ... ከዚኽ ወዴት? ክ.16 (አያልሰው ደሴ)
የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ ስድስት
አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)
ኢዴኃኅ …
ሐ) ምሥረታ፦ የጉባዔው ተሳታፊዎች የአገሪቱን አጠቃላይ ሁኔታ እና ለለውጥ የቆሙ ህዝባዊ (ዴሞክራት) ኃይሎች ቀደም ሲል ትግላቸውን ለማስተባበር መሥርተዋቸው የነበሩ የጋራ መድረኮችን (ሕብረቶችን) ድክመቶች፣ ግድፈቶችና ጠንካራ ጎኖች በዝርዝር፣ በሰከነና በጥልቀት በመመርመር የጋራ ግንዛቤ ጨብጠዋል።
ይኸንን ግንዛቤ ከጨበጡ በኋላ፤ አሁንም በተናጠል በሚያደርጉት ትግል ላይ መቀጠሉ ለሀገራችንና ለህዝቧ ሰቆቃ አለማክተም አስተዋፅዖ ከማድረግ ውጭ ስለማይሆን፤ ሁሉም አትራፊ የሚሆኑበትና ሀገርና ህዝብን የሚጠቅም አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት አንድ ላይ መሰለፍ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን በማጤንና በመቀበል፤ አልፎም ይኽንን አካል (ኢዴኃኅን) መሥርቶ ለመውጣት ሙሉ ስምምነት ላይ በመድረስ፣ ጉባዔው በመጨረሻ ሁለት ቀናት ስብሰባዎቹ የተወያየባቸውን ነጥቦች የትግል ትልምንና ስልትን እንዲሁም የተደረሰባቸው ግንዛቤዎች ላይ የተመሠረተውን የጋራ ራዕይ በተግባር ለመተርጎም የሚያስችል መጣኝ አደረጃጀትን፣ አወቃቀርንና አስፈፃሚ አካላትን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ መሰየምን በተመለከተ ነበር። … (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)



