የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ... ከዚኽ ወዴት? (ክፍል ሰባት - አያልሰው ደሴ)
የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ሰባት
አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)
... ኢዴኃቅ አዲሱ የኢህአዴግ መሪዎች በሀገራችን ላይ የተከተሉትንና ሥራዬ ብለው የተያያዙትን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ቅኝቶች አደገኝነት ጠንቅቆ የተረዳ በመሆኑ እነኛ አደገኛ ውጥኖች በተግባር እንዳይተረጎሙ ከጥንስሱ ጀምሮ በተቻለው መንገድ ሁሉ አምርሮ ታግሏል። ሆኖም በተጠቀሱት ዋና ዋና ምክንያቶች እነኝህን አደጋዎች ማስቀረት ቀርቶ ማዘግየት አልተቻለውም።
ምንም እንኳ በአብዛኛው አባል ድርጅቶቹ አማካኝነት በስውር (በኅቡዕ) በሀገር ውስጥ አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ያልተቋረጠ ጥረቶች ቢያደርግም የኢዴኃቅ ጎላ ያለ አንፃራዊ ጉልበትና እርብርቡም ከሀገር ውጭ ስለነበር እነዚያን እስካሁን የቀጠሉና ሥር እየሰደዱ የመጡ ሀገርና ህዝብ ጎጂ የኢህአዴግ መርኀ-ዕቅዶች ለማስቆም የሚጠይቀውን መሬት የያዘ ጠንካራ ትግል ማድረግ ሁኔታዎች አልፈቀዱለትም። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



