ስለወ/ት ብርቱካን ጠ/ሚ መለስ የማይደፍሩት ሐቅ
ሠላማዊት
ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በአሜሪካው ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ስለወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ሲጠየቁ በየመድረኩ ከሚለዋወጡት ምላሽ አንዱን መለሱ። ”ይቅርታ አልጠየኩም የሚል ሰው በሕጋችን መሠረት ይቅርታው ተነስቶ ውሳኔው ተፈፃሚ ይሆናል አሉ” (ቃል በቃል ስለመጥቀሴ ርግጠኛ አይደለሁም)። የትኛው ሕግ ይህን እንደሚል ግን አንቀጽ ጠቅሰው ማስረዳት አይችሉም። እንዲህ የሚል ድንጋጌ የያዘ አዋጅም ሆነ ደንብ የለም።
ጠ/ሚኒስትሩ ብርቱካን ከታሰረችበት ጊዜ አንስቶ ስለጉዳዩ መጠየቃቸው አልቀረም። ምላሻቸው ግን አንድም ግዜ ተዛምዶ አያውቅም። ሐሙስ መጋቢት 9 ቀን 2002 ዓ.ም. በየተራ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት የተናገሩትን ብንመለከት፤ ሰሞኑን ከተናገሩት ጋር ፈጽሞ አይዛመድም። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



