በዘንድሮው ምርጫ መራሹ ኢህአዴግ

ቁጥር ማከፋፈል ለፓርቲዎች ሲያደርግ

 እሱ የሚወስደው የአሸናፊ ድርሻ

ምን ያህል እንደሆን በስተመጨረሻ

ምርጫ ጣቢያ ሳልሄድ ከቤቴ ሳልወጣ

ውጤቱን አውቃለሁ ስንት እንደሚያመጣ

ወለላዬ ከስዊድን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ከዚህ ቀደም ለአንድ ዓመት በየሣምንቱ ”የረቡዕ ግጥም” ለሃምሳ ሁለት ሣምንታት ”ወለላዬ” በሚል የብዕር ስም የሚታወቀው ገጣሚ ማትያስ ከተማ ሲያቀርብልን መቆየቱ ይታወሳል። የሁለተኛ ዓመቱን የረቡዕ ግጥም ከላይ ባስነበብነው ግጥም የጀመረ ሲሆን፣ ከሚቀጥለው ሣምንት ጀምሮ ዘወትር ረቡዕ አንድ ግጥም ጀባ ይለናል። በአንባብያን/ትና በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ስም ገጣሚ ማትያስን በዚህ አጋጣሚ ልናመሰግን እንወዳለን። የረቡዕ ሰው ይበለን! - አሜን!!!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ