ውዴ ውበትሽ (ገ/ኢ. ጐርፉ)
ገ/ኢ. ጐርፉ
ውበትሽ አክለፍልፎኝ
ድቅን ብሎ እየታየኝ
ከሰው ሁሉ አላክፎኝ
እንደ አውሬ በርሃ ለየኝ።
ውዴ ውበትሽ ለኔ
እንደ ፀሐይ ከዋክብት
አለው ምስጢራዊ ቅኔ
የልብ፣ የጉበት፣ የክት።
የዓይኖችሽ ቦግታ
መላ ልቤን ያበራል፣
ስንጫወት በዝግታ
ሕይወት ምንኛ ያምራል።
ገ/ኢ. ጐርፉ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



