ባላባት ወይ ሎሌ (ያምሮት አወቀ)
ያምሮት አወቀ
ድንበሬን ስጠብቅ ከጠላት ወረራ
ነፃ ላውጣ ብዬ ሀገሬን ላስጠራ
ሳስገብር ሀገራት ጠረፍ ተላልፌ
ልገነጠል ብዬ ድንበሬን አጥሬ
አዲስ ስም አፍልቄ ሀገርን ፈጥሬ
ይሄ ክልሌ ነው ውጣ ከመንደሬ
በመካለል እንጂ ያገር ክፋይ ቀርቶ
ተከላክሎ ፍቅርን ተከልሎ ኑሮ
ሁሉም ጥጉን ይዞ አያገባኝም ብሎ
ይላል አይገባም የሰው ጓሮ ዘሎ
በዚህ መሬት ጉዳይ ስንት ግዜ ሞትኩኝ
ስንት ግዜ ቆሰልኩኝ ምን ያህል ገደልኩኝ?
የፈሰሰ ደሜ መሬት ሲያረሰርስ
የቆመው አጥንቴ አፈሩን ሊመግብ ደቆ ሲከሰከስ
ስጋዬ አፈር ሆኖ ወደ አፈር ሲመለስ
ያኔ ተረዳሁኝ ያኔ ገና ገባኝ
መሬቱ ነው ጌታ ለካ እኔ ሎሌው ነኝ
ያምሮት አወቀ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



