ሳለህ ኦምራን
ድሮ የዛሬ ሃምሳ አመት
አፍሪካን አንድ እናርግ ብለው ለተነሱት
ዘር አጥንት ቀለምን
ዘመድ ጎራ ቋንቋን
ነገድን ሳይለዩ አንድ እንሁን ብለው
ቆመው ላቋቋሙት


አፍሪካዊነትን ዘምረው ላዜሙት
ላፍሪካ ደህንነት ጊዜ ለከፈሉት
ላላማቸው ስኬት ህይወት ለገበሩት
የዛን ዘመን ብሶት የዛን ዘመን ተንኮል
ገፈቱን ቀማሾች መከራን ለቻሉ
መሪ ተመሪውም ምሁር ሊቃውንቱ
እስኪ እንክፈላችው
ብንችል አፍሪካን ባንችል ክፍሏን
እኩልነት ስፍኖ ፍርድ የተሳኩባት
ምሁራን ሳይፈልሱ አዋቂ ሳይፈራት
ሃብቷ ሳይመዘበር ንብረቷ ሳይሸሻት
እንኳን ለስው ልጆች ለእንስሳቷ ክብር
የስጠች እናርጋት በይቻላል ምክር
ህግ የበላይ ሆኖ
ትርጉሙ እኩል ሆኖ
ዙልም ግፍን ፈርቶ
ህሊናን ቅን ገርቶ
መሪነት በሥራው በግብሩ ተከብሮ
ይሥራልኝ ያለውን ከቦታው አስፍሮ
እንያት አፍሪካን ዴሞክራሲ ሰፍሮ


ሳለህ ኦምራን
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ