አባዩ አባይ
ያምሮት አወቀ
አባይ ሊገደብ ነው ፈርኦን ተቆጣ
ደንፋ ኮራ አልኩኝ ዘራፍ ታ-ታ-ታ
ፎክሬ ፎክሬ ደንፍቼ ስነቃ
አባይን ገደቡት በደሜ በስጋ
አባይ ለዛው ጠፍቶአል
ሞተር ጄነረተሩ አዋክቦ ይዘውታል
ውበቱ ተማጦ ማረጉ ተነፍጓል
አባይ በኮረንቲ እዛ ማዶ አድምቋል
ምነዋ እዚ ማዶ ጨለማ የዋጠኝ?
ባባይ ልጅነቴ ውሀ የሚጠማኝ?
ጠየኩት አባይን እንዲያመላክተኝ
አባይ ተከዝ ብሎ ተገድቤ ያለሁ
ላልፍባችሁ እንጂ መቼ ሆነ ነገሩ ላሳልፍላችሁ
ያምሮት አወቀ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



