ሲ ... መለስ (ልጅ ስምኦን)
ሲ ... መለስ
ልጅ ስምኦን ከፓሪስ
ያ ዳገት ነው ሲሉኝ ወጣሁኝ አቀበት
ያ ገደል ነው ስባል ወረድኩኝ ቁልቁለት
ይዤ ሳልጨብጠው ነብሴን ስሳሳለት
ወጥቼ እንዳልወርድ!! ግን ወረድኩ በቅፅበት
ላይደላኝ ቀን ሞልቶ ሰውም ቀኔን አይቶ
ጨለማውም ነግቶ ሊወስደኝ አድብቶ
ሳልነቃ ከለሰኝ ላይምረኝ አሟርቶ
ብመጣም እሄዳለሁ ካልሄድኩም እመጣለሁ
እሱ ከፈቀደ ቢጎድልም ሙሉ ነው
ልሂድ አላልኩም በሩን አንኳኩቼ
ሲምጣም ልሄድ ነው አለምን ጎብኝቼ
አፄው ሲያንቀላፋ ጉልተኛው ሲለፋ
ሲዳክር ሲነሳ
ሲያልም በተስፋ
ማነው የኛ ጀግና ዘውዱን የሚደፋ
ግራኝ በቀኝ ዘምቶ
ያሻውን አድምቶ
ያጣውን አግኝቶ
ግኝቱ ሰንብቶ
ፊት ለነብሱ ሳስቶ
ደጁንም መክቶ
ዝማሬ በርክቶ
ላይድን መላክ አይቶ
ሲመጣም ሊሄድ ነው አለምን ጎብኝቶ
ልጅ ስምኦን ከፓሪስ



