ያኔ

ካሣ በ. በላይ

መርሳትስ ብጀምር አርጅቼ ጃጅቼ

አንድ ዘፈን ባስታውስ ሌሎቹን ረስቼ

በተሰበረ ድምፅ ያንን ባንጎራጉር

ነግቶ እስኪመሽም እእ ... ህህ ... ምም... ስል ብውል

 

ዓተርን መቆርጠም አጥንትም ቢያቅተኝ

እንዲያው ይባስ ብሎ መብላት ቢታክተኝ

ጥርሴ ሁሉ ወልቆ ድዴም ቢሻግት

ጉልበቴ ተዳክሞ ወኔዬም ቢሞት

አፌ ተቆላልፎ መናገርም ባልችል

"እፍ" ... "እስ" ቢያሰኘኝ "ፕ" እላለሁኝ ስል

 

ደክሞና ደብዝዞ አላይ ሲለኝ ዓይኔ

ደጋፊና መሪ ስፈልግ ከጎኔ

"አይዞህ፣ አለሁልህ!" ትይኛለሽ ያኔ?

 

አልራመድ ሲለኝ እግሬም ለግሞ

አጎንብሼ ስሄድ ወገቤ ተጣሞ

ሳዘግም ስጎተት ምርኩዝ ብጤ ይዤ

ትወጂኝ ይሆን ወይ ያን ጊዜ፣ ያን ጊዜ!

 

ቢጸናብኝና ጆሮየም ባይሰማ

ነገር ብቀላቅል ከሰው ባልስማማ

ቁጣ ቁጣ ቢለኝ ቢወጣኝ ኃይለ ቃል

ያኔ ... ያኔ ... ፍቅርሽ ያልቃል?

ለኔስ ያለሽ ስሜት ያበቃል?

ወይስ ከዛም አልፎ ይዘልቃል?


ካሣ በ. በላይ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ