አልነጋም- ገና ነው! (ዳግማዊ ዳዊት)
አልነጋም- ገና ነው!
ዳግማዊ ዳዊት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
የሰማይ ኮርኒሥ ሆኖ - ማቅ የመሰለ ደመና
ከታችም አውሎ ነፋስ - ፉጨቱን እያሰማ
አቧራውን አስነስቶ - ዛፍ ቅርንጫፉን እያሾረ
ዛሩ እንደወረደ ባለአውሌ - አለመጠን እያስጨፈረ
ዓይን ቢወጉ በማያሳይ - ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ
ወዴት ነው መድረሻችን - ጉዟችን የሚያቀና?
ትናንት እንዳስቆመን ዝናብ - ሊዘንብ ሰማዩ አግቶ
ወዴት ነው የምንሄደው - በትናንቱ ምን ታይቶ?
ትርምስምሳችን ወጥቶ - ጨቅይቶ ሳለ መንገዱ
ለይምሰል አይሆንም ወይ - ደግመን ዛሬ መሄዱ?
ትናንት መካሪ ጠፍቶ - ሌሊቱ ገና እንዳልነጋ
ጉዞው መርዛም - እሾክ በዝቶበት - ስንቱ ነው የተወጋ?
እኔስ አልምክርውም- የዛሬውን መንገድ
እስኪነጋ እቆያለሁ - ካልሆነብኝ የግድ
አልነጋም ገና - ጨለማ ነው ሌሊት
እነሱንም ንገሩዋቸው - መጓዙን ይተዉት
ተከታያቸውን በመሉ - የአውሬ ቀለብ አያርጉት።
ዳግማዊ ዳዊት
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ጥር 2002 ዓ.ም.



