በ’ንባዬ ልሸኝሽ !(አስራደው - ከፈረንሳይ)
በ’ንባዬ ልሸኝሽ !
አሥራደው (ከፈረንሳይ)
በሰው አገር ሆነሽ አገር እንደራበሽ፤
እናት አባት ናፍቀሽ፤
ወንድም እህት ናፍቀሽ፤
ብለን ስንጠብቅ አገር ትገቢያለሽ፤
በዚያው ቀረሽ ምነው ናፍቆትሽን ይዘሽ ?
ጥቂትም ሳታርፊ በሰው አገር ለፍተሽ፤
በሥጋ እንደበረርሽ በነፍስሽም ቀጠልሽ፤
እቴ ያገሬ ልጅ ከልቤ አዘንኩልሽ፤
ሌላ ምን ሃብት አለኝ በ’ንባዬ ልሸኝሽ ::
በአይሮፕላን አደጋ ሕይወታቸው ላለፈ እህቶቻችን መታሰቢያ



