የአውራዎች አንድነት (ዳግማዊ ዳዊት)
የአውራዎች አንድነት
ዳግማዊ ዳዊት (ጥቅምት 2002 ዓ.ም) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ጃርት የሚባል አውሬ - ግፍ ቢያበዛበቸው
ንቦቹ ወጡና - ከየመኖሪያቸው
ጥያቄ አቀረቡ - ለየአውራዎቻቸው።
ስብሰባ - ቁጭ አሉ፣
በስፋት - መከሩ።
አውራዎቻቸውን - ፊት ለፊት ቁጭ አርገው
እንዲህ ነገሩዋቸው
እንዲተባበሩ
መሪዎቹ ሁሉ
አውራዎች በሙሉ - በአንድነት ከሰሩ
ክፉ ጃርት አይመጣም - በዚህ በሰፈሩ።
ቃልም ተገባቡ - ከዚህ ቃል ላይወጡ፣
ለአናቢው ገበሬ - ትዕዛዝንም ሰጡ
አንተ ንብ አናቢ - ከዛሬ ጀምረህ
አሳየን ብለናል - በአንድ ቀፎ አድርገህ።
አናቢው ገበሬ - ልቡ እያመነታ
ትናንት በሚያውቀው - በለመደው ፋንታ
አንድ ቀፎ መርጦ - በጭስ አጠነና
ንቦችን በመሉ - ከአውራዎቹ ጋራ
በአንድ አስቀመጣቸው
እንደጥያቄያቸው።
…
ያለ አፈጣጠሩ
ሆኖ ትብብሩ
እያንዳንዱ መሪ - ሠራዊቱን ይዞ
ቀፎው ባዶ ቀረ - ንብ ሁሉ ተጉዞ።
ድሮም ሆኖ አያውቅም፣
ትናንት ሆነ ዛሬም
አንድ የንብ አውራ ነው - ከሺህ ሠራዊት ጋር
ውጤትን የሚያሳይ - የሚጋግረው ማር።
ዳግማዊ ዳዊት
ጥቅምት 2002 ዓ.ም.
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



