Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥቅምት 22 ቀን 2001 ዓ.ም. November 1, 2008)፦ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ የሚመራው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዲን) ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ በቀለ ጅራታ ባልታወቀ ምክንያት ከቤታቸው ተወስደው መታሰራቸው ታውቋል።

 

ዋና ፀሐፊው አቶ በቀለ ትናንት ዓርብ ጥቅምት 21 ቀን ጧት ፖሊሶች በመኖሪያ ቤታቸው መጥተው ፍተሻ ካካሄዱ በኋላ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ሦስተኛ) ተወስደው መታሰራቸውን አቶ ቡልቻ ገልጸዋል።

 

አቶ ቡልቻ እንዳሉት አቶ በቀለ በቤታቸው ላይ ከፍተኛ ፍተሻ ተደርጎ ከቤታቸው ተወስደው ነው የታሰሩት። በተጨማሪም በምን ምክንያት እንደታሰሩ የታወቀ ነገር አለመኖሩን እና እስካሁንም ጠበቃ ገብቶ እንዳላነጋገራቸው የፓረቲው ሊቀመንበር አቶ ቡልቻ ገልፀዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ