በመጨረሻም ሕወሓት እና ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ተላለፈ
ሕወሓት
ውሳኔው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው
ኢዛ (ቅዳሜ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 1, 2021)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው ስብሰባ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና ኦነግ ሸኔ ላይ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቦ ውሳኔ ተላለፈ።
በሁለቱ ድርጅቶች ላይ በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ያስገደዱ ተግባሮቻቸውን በመዘርዘር የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ባወጣው አዋጅ መሠረት ድርጅቶቹ በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቧል።
በተመሳሳይ ተግባር በተሰማሩ እና በዚህ ውሳኔ ሐሳብ መሠረት ከተሰየሙት የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ትብብር፣ ትስስር ወይንም የሐሳብ እና የተግባር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም ይህ ውሳኔ ተፈጻሚ ይኾናል ተብሏል። (ኢዛ)



