ኮሎኔል ጌትነት አዳነ

ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፣ የአገር መከላከያ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር

ወደቀያቸው ለሚመለሱ ሠራዊቱ ሙሉ ጥበቃና እገዛ እንደሚያደርግ አስታውቋል

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. April 30, 2021)፦ በቅርቡ በታጣቂ ኃይሎች ሙሉ በሙሉ ከወደመችው የአጣየ ከተማ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደቀያቸው እንዲመለሱ የአገር መከላከያ ጥሪ ማቅረቡን እና ወደቀያቸው ለሚመለሱ ሁሉ ሠራዊቱ አስፈላጊውን ጥበቃ እና ድጋፍ እንደሚያደርግም የአገር መከላከያ አስታወቀ።

የአገር መከላከያ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በአጣየ ከተማ የነበረው የጸጥታ ችግር ወደ ሰላም እና መረጋጋት በመመለሱ፤ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እንዲመልሱ ዛሬ (ዓርብ ሚያዝያ 22 ቀን 2013 ዓ.ም.) በሰጡት መግለጫ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የአጣየ ከተማ የጸጥታ ችግር በአገር መከላከያ ሠራዊት እና በሌሎች የጸጥታ አካላት በትብብር ባደረጉት የጸጥታ ማስከበር ሥራ በአሁኑ ወቅት አካባቢው ወደ ሰላም እና መረጋጋት መመልሱን የተናገሩት ኮሎኔል ጌትነት፤ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደቀያቸው እንደመለሱ ጥሪ ከማድረግ ባሻገር፤ ለሚመለሱት ተፈናቃዮች ሠራዊቱ ሙሉ ጥበቃ እና ድጋፍ እንደሚያደርግላቸውም ማረጋገጫ ሰጥተዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ