አሜሪካ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር ውስጥ አልገባም አለች
ታላቁ የህዳሴ ግድብ
በአደራዳሪነት ለመግባት የሦስቱንም አገሮች ይሁንታ ትፈልጋለች
ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 18, 2021)፦ አሜሪካ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሦስቱ የተፋሰሱ አገሮች በሚያደርጉት ድርድር ውስጥ ከዚህ በኋላ ካልተጠየቅኹ በአደራዳሪነት አልገባም ማለትዋ ተሰማ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቀጠናዊ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ለአንድ ለግብጽ ቴሌቭዥን እንደገለጹት፤ ሦስቱም አገራት (ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ) አሜሪካንን ካልጋበዝዋት በስተቀር፤ ለማደራደር ጣልቃ አትገባም ብለዋል።
ነገር ግን ከሦስቱም አገራት ጥሪ ከተደረገላት፤ አሜሪካ የሚጠበቅባትን አወንታዊ ሚና ለመጫወት ዝግጁ ስለመኾንዋ ያመለከቱት ቃል አቀባዩ ሳሙኤል ዋርበርግ፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የሚመለከቱ አለመግባባቶች መፈታት ያለበት በሦስቱ አገራት ብቻ ስለመኾኑ ጠቁመዋል። (ኢዛ)



