በጄኔቭ (ስዊዘርላንድ) ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ዝናብ እየወረደባቸው ድምፃቸውን ሲያሰሙ

በጄኔቭ (ስዊዘርላንድ) ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ዝናብ እየወረደባቸው ድምፃቸውን ሲያሰሙ

ከሕወሓት ደጋፊዎች የሚቀርቡ የተሳሳቱ መረጃዎችን ይዘው እነ ተመድ፣ አውሮፓ ሕብረትና አሜሪካ እያወጡ ያሉትን መረጃ እንዲመረምሩ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል

ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 15, 2021)፦ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ለማሳወቅ እና በተሳሳተ መረጃ በኢትዮጰያ ላይ ጫና ለማሳደር እየተደረገ ያለውን ጥረት የተቃወሙ በስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጄኔቭ ጎዳና ድምፃቸውን አሰሙ።

የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲክበርና በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ አካላትን የሚያወግዙ መልእክቶች በተላለፉበት በዚህ ትዕይንተ ሕዝብ፤ ኤርትራውያንም የተሳተፉበት ነበር። በዚህ ሰልፍ ላይ የሕወሓት ደራፊዎች እያሰራጩ ያሉትን ሐሰተኛ መረጃ በመያዝ፤ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደርግ የሚደረገውን ጥረት ሰልፈኞቹ በእጅጉ አውግዘዋል።

ይህ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ እየተካሔደ ያለውን ከሕወሓት ደጋፊዎች የሚቀርቡትን የተሳሳቱ መረጃዎች ይዘው እንደ ተባበሩት መንግሥታት፣ የአውሮፓ ሕብረት እና አሜሪካ እያወጡ ያሉትን መረጃ እንዲመረምሩና ትክክለኛውን መረጃ በመውሰድ አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ ጠይቀዋል። እንደ ጄኔቩ ሰልፍ ሁሉ ተመሳሳይ ዓላማ ያለው ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ መካሔዱ አይዘንጋም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ