Journalist Getachew Tedla

አንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ተድላ

ከ36 ዓመት በላይ ለጀርመን ራዲዮ አገልግሏል

ኢዛ (ሐሙስ ነኀሴ ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 20, 2020)፦ በውጭ መገናኛ ብዙኃን ዘጋቢነት በመሥራት ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ የሚታመንለት አንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ተድላ የቀብር ሥርዓት ዛሬ ሐሙስ ነኀሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ተፈጽሟል።

በዶቼቬሌ ራዲዮ ከዕድሜው እኩሌታ በላይ በአዲስ አበባ የጣቢያው ዘጋቢ በመኾን ሲያገለግል የቆየው የጋዜጠኛ ጌታቸው ሥርዓተ ቀብሩ በጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።

ባደረበት ሕመም በ67 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ጋዜጠኛ ጌታቸው ተድላ፤ በጀርመን ራዲዮ ብቻ ከ36 ዓመት በላይ ያገለገለ ሲሆን፤ ለዚህን ያህል ዓመት ለውጭ ሚዲያ ከአዲስ አበባ የዘገበ ጋዜጠኛ እንደሌለ ይነገራል።

በጋዜጠኛ ጌታቸው ሕልፈተ ሕይወት የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል ኀዘኑን እየገለጸ፤ ለመላው ቤተሰቦችና ወዳጆቹ መጽናናትን ይመኛል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ