Our green legacy continues, Ethiopia 2020

አረንጓዴ ዐሻራችንን ማሳረፋችንን እንቀጥላለን፤ ችግኝ ተከላ 2012

ባለፈው ዓመት ከተተከሉት አራት ቢሊዮንች ችግኞች ውስጥ 80 በመቶው ጸድቋል

ኢዛ (ዓርብ ግንቦት ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 5, 2020)፦ ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሪኮርድነት የተያዘና የአራት ቢሊዮን ችግኝ ተከላ ማካሔድ የቻለችው ኢትዮጵያ፤ ዘንድሮም አምስት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው መርኀ ግብር ዛሬ ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ ይጀመራል።

የዘንድሮው የአምስት ቢሊዮን ችግኝ ተከላ ዛሬ እንደሚጀመር ከትናንት በስቲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በዚሁ መርኀ ግብር ዙሪያ በተሰጠው መግለጫ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ቀን፣ የችግኝ ተከላ መርኀ ግብር በዛሬው ዕለት በአዋሳ አካባቢ በታቦር ተራራ ላይ ይጀመራል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ትናንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፤ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርኀ ግብር ከኮሮና መከላከል ጥንቃቄ ጋር ተጣጥሞ የሚካሔድ መኾኑን ነው።

በሁሉም ክልሎች ተፈፃሚ የሚኾነውን ይህን ችግኝ ተከላ ለማካሔድ በሁሉም ክልሎች የችግኝ ዝግጅት እየተደረገ መቆየቱ ይታወሳል። በመንግሥት መግለጫ ባለፈው ዓመት ከተተከለው አራት ቢሊዮን ችግኝ ውስጥ 80 በመቶው ጸድቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ