የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF)

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ)

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና አቀረቡ

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 1, 2020)፦ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት የሚውል የ411 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ የሚያስችለውን ውሳኔ አጸደቀ።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ቦርድ በድርጅቱ አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ አሠራር ማዕቀፍ በኩል ድጋፉን የሚሰጥ መኾኑንም ዛሬ ባወጣው ሪፖርቱ አስታውቋል።

እንደ አይ.ኤም.አፍ የዛሬ መረጃ ተቋሙ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለ መኾኑንና እንደ አስፈላጊነቱ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ፤ እንዲሁም በፖሊሲ ጉዳዮች የምዘና ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ነን ብሏል። የአይኤምኤፍ ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ታኦ ዣንግ የአይኤምኤፍን ውሳኔ ተከትሎ በሰጡት አስተያየት፤ የግል ዘርፍ ሚና ለማጐልበት ከአይኤምኤፍ የወሰደቻቸውን የገንዘብ ድጋፍ በአግባቡ ተጠቅማ ለውጥ አምጥታለች።

ዛሬ ይፋ የተደረገውንና አይኤምኤፍ ያጸደቀውን የገንዘብ ድጋፍ በተመለከተ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በፌስቡክ ገጻቸው አይኤምኤፍ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ብቃት ለተሞላበት አመራራቸው ወረርሽኙን ለመከላከል ከኢትዮጵያ ጐን በመቆማቸው አመስግነዋል። አያይዘውም የአይኤምኤፍ ቦርድ በድርጅቱ ፈጣን የገንዘብ ድጋፍ አሠራር ማዕቀፍ አማካኝነት ለኢትዮጵያ በእጅጉ የሚያስፈልጋትን 411 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉ፤ ኢትዮጵያ በዘርፉ የሚያስፈልጋትን የገንዘብ መጠን መቶ በመቶ የሚሸፍን ነው ብለዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ