ስካይላይት ሆቴል ለገቢ መንገደኞች የለይቶ ማቆያ ይኾናል
ስካይላይት ሆቴል፣ አዲስ አበባ
ለ14 ቀን በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ አለባቸው
ኢዛ (ቅዳሜ መጋቢት ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 21, 2020)፦ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞችን ለ14 ቀን ለይቶ ለማቆየት የተሠጠውን የመንግሥት ውሳኔ ተከትሎ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለለይቶ ማቆያው በስሩ የሚተዳደረውን ስካይላይት ሆቴል አንዱ ማቆያ እንደሚኾን ገልጿል።
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ትናንት መንግሥት በደረሰበት ውሳኔ መሠረት፤ ገቢ መንገደኞቹ የ14 ቀን ወጪያቸው ራሳቸው በመሸፈን በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ አለባቸው ማለቱን መዘገባችን አይዘነጋም። (ኢዛ)



