የተቋረጠው የአገር ውስጥ በረራዎች ቀጠሉ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ወደ ደሴ የሚያደረገው በረራ መስተጓጎሉ ተገለጸ
ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 17, 2020)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ፀባይ ምክንያት ተስተጓጉሎ የነበረውን የመቀሌ፣ የባህር ዳር፣ የላሊበላ፣ የጐንደር፣ የሁመራ፣ የአክሱምና የሽሬ በረራዎች መልሶ መጀመሩን አስታውቋል።
አየር መንገዱ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም. ወደ እነዚህ ከተሞች የነበረውን በረራ በአየር ፀባይ ምክንያት አቁሞ የነበረ ሲሆን፤ ትናንት መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ግን መልሶ መጀመሩን ገልጿል። ወደ ደሴ ያደርግ የነበረው በረራ ግን መታጐሉን የገለጸው አየር መንገዱ የአየር ፀባዩ እንደተስተካከለ የደሴውም በረራ ይቀጥላል ብሏል። ለተፈጠረው ችግም አየር መንገዱ ይቅርታ ጠይቋል። (ኢዛ)



