ፊሕዴ

የፊንፊኔ ሕዝቦች ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (ፊሕዴ) - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ ለሦስት ወር የሚቆየውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድና እውቅና ከተሠጣቸው 11 ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ ፈቃድ የተሠጠው ጥር 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው።

ለአሥራ አንዱ ጊዜያዊ እውቅና ሠጥቷል

ኢዛ (ማክሰኞ የካቲት ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 18, 2020)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለስድስት ፓርቲዎች የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሲሠጥ፤ ለአሥራ አንድ ፓርቲዎችም የሦስት ወር ጊዜያዊ እውቅና መሥጠቱንም ገልጿል።

ቦርዱ ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ የምዝገባና ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (ሰርቲፊኬት) ከተሠጣቸው ስድስቱ ፓርቲዎች ውስጥ አራቱ አገር አቀፍ ሲሆኑ፤ ሁለት ክልላዊ ናቸው። ስድስቱም ፓርቲዎች ስም፣ አገር አቀፍ ወይም ክልላዊ መኾናቸው፣ እንዲሁም የምስክር ወረቀቱ ከተሠጣቸው ቀን ዝርዝር ጋር እንደሚከተለው ቀርበዋል።

ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኅብር ኢትዮጵያ) - የአገር አቀፍ ፓርቲ ኾኖ የምስክር ወረቀቱ የካቲት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ተሠጥቶታል፣
መላው አማራ ሕዝብ ፓርቲ (መአሕፓ) - የአገር አቀፍ ፓርቲ ኾኖ የምስክር ወረቀቱ የካቲት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ተሠጥቶታል፣
ነፃነትና ሰላም ለኢትዮጵያ ሕብረት ፓርቲ (ነለሰላም) - የአገር አቀፍ ፓርቲ ኾኖ የምስክር ወረቀቱ የካቲት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ተሠጥቶታል፣
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊና ፍትሕ (ኢዜማ) - የአገር አቀፍ ፓርቲ ኾኖ የምስክር ወረቀቱ ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ተሠጥቶታል፣
አፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ (አነግፓ) - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ የምስክር ወረቀቱ ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ተሠጥቶታል፣
የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ቦዴፓ) - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ የምስክር ወረቀቱ ጥር 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ተሠጥቶታል።

እንደቦርዱ መረጃ ለሦስት ወር የሚቆየውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድና እውቅና የተሠጣቸው 11 ፓርቲዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ አገራዊ ሲኾኑ የተቀሩት ሰባቱ ደግሞ ክልላዊ ናቸው። የ11ዱ ፓርቲዎች ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ነው፤

ኤጀቲማ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ኤፌፓ) - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ፤
ሱማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም.፣
የካፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት (ካሕዴሕ) - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም.፣
የፊንፊኔ ሕዝቦች ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (ፊሕዴ) - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው ጥር 21 ቀን 2012 ዓ.ም.፣
የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርት - አገር አቀፍ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው ጥር 21 ቀን 2012 ዓ.ም.፣
ሕብረት ለዴሞክራሲና ለነፃነት ፓርቲ (ሕዴነፓ) - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው ጥር 21 ቀን 2012 ዓ.ም.፣
የሲዳማ አንድነት ፓርቲ (ሲአፓ) - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው ጥር 21 ቀን 2012 ዓ.ም.፣
ኢትዮጵያ አገር አቀፍ ፓርቲ - አገር አቀፍ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው የካቲት 4 ቀን 2012 ዓ.ም.፣
የሶማሌ ብሔራዊ ፓርቲ (ሶብፓ) - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው የካቲት 4 ቀን 2012 ዓ.ም.፣
የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር (ኢአአግ) - አገር አቀፍ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው የካቲት 4 ቀን 2012 ዓ.ም፣ እንዲሁም
የወለኔ አርሶ አደር ሕብረት - ክልላዊ ፓርቲ ኾኖ ፈቃድ የተሠጠው የካቲት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ጊዜያዊውና ለሦስት ወር የሚቆየው የምዝገባ ፈቃድና እውቅና የተሠጣቸው ፓርቲዎች መኾናቸው ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ