Office of the Prime Minister

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ይኽኛው ሲታከልበት የያዝነው ዓመት በጀት 414.84 ቢሊዮን ብር ይደርሳል

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 17, 2020)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተጨማሪ 27.89 ቢሊዮን ብር በጀት እንዲፈቀድ የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አጽድቆ ለፓርላማ ላከ። ይኽኛው ሲታከልበት የያዝነው ዓመት በጀት 414.84 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን ባካሔደው ስብሰባ፤ ገንዘብ ሚኒስቴር ተጨማሪ በጀቱ እንዲፈቀድለት የጠየቀው ለአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መኾኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ኢኮኖሚው አሁን ከገጠመው ተግዳሮቶች የሚላቀቅበትን የፖሊሲ እርምጃዎች ተግባራዊ ለማድረግ እንደኾነ በመጥቀስ፤ ለዚሁ 18 ቢሊዮን ብር፣ ለልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ትግበራ ሁለት ቢሊዮን ብር፤ እንዲሁም ለእኩል ሥራ እኩል ደምወዝ አገራዊ ትግበራ 7.89 ቢሊዮን ብር፤ በድምሩ 27.89 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ተጠይቆ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አጽድቆታል።

ይህም በ2012 ዓ.ም. ለአገሪቱ ከተያዘው ዓመታዊ በጀት በጭማሪነት የሚያገለግል ይኾናል። መንግሥት በፓርላማ ያጸደቀው የ2012 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት 386.95 ቢሊዮን ብር እንደነበር አይዘነጋም።

ይኼ የተወሰነው ተጨማሪ በጀት ሲታከል፤ በበጀት ዓመቱ የተያዘውን በጀት 414.84 ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ