ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ይዘዋቸው ከተመለሱት ለአንዷ ሰላምታ ሲሠጡ

ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ይዘዋቸው ከተመለሱት ለአንዷ ሰላምታ ሲሠጡ፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ

ከአሥር ሺህ በላይ ሕጋዊ መረጃ ላልነበራቸው ኢትዮጵያውያን የቪዛና የሥራ ፈቃድ እንዲያገኙ ተደርጓል

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 16, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በመጓዝ ከኢትዮጵያውያን ጋር የነበራቸውንና በተያያዘ ሥራ አጠናቅቀው ሲመለሱ፤ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ ከአገር እንዳይወጡና ከፍተኛ ችግር ውስጥ የነበሩ 137 ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በማስጨረስ፤ ወደ ኢትዮጵያ ይዘው ተመልሰዋል።

ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ ጋር በመነጋገርና በማስፈቀድ ኢትዮጵያውያኖቹ ምሕረት እንዲደረግላቸው በማድረግ፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ሌሎች በዚያ የሚገኙና ከ10 ሺህ በላይ የሚኾኑ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በተለያዩ መጠለያዎች ያሉ ኢትዮጵያውያን በሕጋዊ መንገድ መንቀሳቀስ እንዲችሉ የተፈቀደ መኾኑ ታውቋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ይዘዋቸው ከተመለሱት ጋር ውስጥ ልጇን ያቀፈች እናት
ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ይዘዋቸው ከተመለሱት ጋር ውስጥ ልጇን ያቀፈች እናት

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሠጡት አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ፤ እነዚህ ሕጋዊ መረጃ ያልነበራቸው ኢትዮጵያውያን ቪዛ እንዲያገኙ ጭምር የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ የተፈቀደ ሲሆን፤ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የሚሹም ኾነ እዚያው መሥራት ለሚፈልጉ እድሉ ተመቻችቶላቸው የሥራ ፈቃድም እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል። (ኢዛ)

ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ይዘዋቸው ከተመለሱት ጋር በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ
ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ይዘዋቸው ከተመለሱት ጋር በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ