Ethiopia's electoral body seeks verification of Jawar Mohammed's citizenship

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ እንዲሠጠው የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲን ማብራሪያ የጠየቀበት ደብዳቤ

ኦፌኮ አቶ ጃዋርን ኢትዮጵያዊ ነው ብሎ የጠቀሰውን ሕግ አንስቷል

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 12, 2020)፦ በአቶ ጃዋር መሐመድ የዜግነት ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ እንዲሠጠው የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲን ማብራሪያ ጠየቀ። ኦፌኮ አቶ ጃዋር ኢትዮጵያዊ ነው ብሎ የጠቀሰውን ሕግ በዚሁ ማብራሪያ እንዲሠጠው በላከው ደብዳቤ ላይ አንስቷል።

በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ በተፈረመ ደብዳቤ ኤጀንሲው ማብራሪያ እንዲሠጥበት የጠየቀበት ዋነኛ ጉዳይ፤ የሌላ አገር ዜግነት ያለው ሰው መደበኛ ኑሮውን በኢትዮጵያ ካደረገ፣ የሌላ አገር ዜግነቱን ከተወና ኢትዮጵያዊ ዜግነቱ እንዲመለስለት ካመለከተ፤ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን በኤጀንሲው ውሳኔ ወዲያውኑ ያገኛል ወይስ አያገኝም የሚል ነው።

በዚሁ ጭብጥ መነሻነት ኤጀንሲው እስከ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ዝርዝር ማብራሪያውን እንዲልክለትም ጠይቋል።

በዚህ ደብዳቤ ላይ “ኦፌኮ አቶ ጃዋርን ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን ለማግኘት ሒደት ላይ እያሉ አባል አድርጎ ኢትዮጵያዊ የሚል መታወቂያ ሠጥቷል” የሚል መነሻ ምክንያት በመሥጠት ያትትና፤ ኦፌኮ አቶ ጃዋር “ኢትዮጵያዊ ዜግነት አግኝቷል” ሲል ሕግን ጠቅሶ ለምርጫ ቦርዱ በሠጠው ምላሽ ላይ ያቀረበውን ሐሳብ በመንተራስ፤ ኤጀንሲው ማብራሪያ እንዲሠጠው ጠይቋል።

አቶ ጃዋር ወደ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ በየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ እንደማይገባ ሲገልጽ ቆይቶ፤ በያዝነው ዓመት ታኅሣሥ ወር ሦስተኛ ሣምንት ላይ ኦፌኮን ስለመቀላቀሉና ኦፌኮም ይህንን ያረጋገጠ መረጃ መሥጠቱን መዘገባችን አይዘነጋም።

ምርጫ ቦርድ የአቶ ጃዋርን የዜግነት ጉዳይና ኦፌኮ አቶ ጃዋር ኢትዮጵያዊ መኾኑን በመግለጽ ለቦርዱ የሠጠውን ምላሽ ላይ ተንተርሶ፤ ቦርዱ ኤጀንሲውን ማብራሪያ የጠየቀበት ሙሉ ቃል የሚከተለው ነው። (ኢዛ)

ጃዋር መሐመድ
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲን የላከው ደብዳቤ ገጽ 1
ጃዋር መሐመድ
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲን የላከው ደብዳቤ ገጽ 2

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ