Tirunesh Dibaba & Sileshi Sihineአትሌት ቀነኒሳ ያሸነፈው የባለቤቱ ስም በተጻፈበት ጫማ ነው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነኀሴ 13 ቀን 2000 ዓ.ም. August 19, 2008)፦ እጮኛሞቹ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ እና አትሌት ስለሺ ስኅን ከቤጂንጉ ኦሎምፒክ መልስ ሀገር ቤት ጋብቻቸውን እንደሚፈጽሙ ታወቀ። አትሌት ቀነኒሳ 10,000 ሜትሩን የሮጠበት ጫማ ላይ የባለቤቱን ስም አጽፎ ነበር።

 

በ10 ሺህ ሜትር በአትሌት ደራርቱ ቱሉ ተይዞ የነበረውን የኦሎምፒክን ክብረወሰን በመስበር ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ እና በዚሁ ርቀት በወንዶች ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ስለሺ ስኅን ከኦሎምፒክ መልስ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ጋብቻቸውን ይፈጽማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለመረዳት ተችሏል።

 

አትሌት ጥሩነሽ የ23 ዓመት ዕድሜ ያላት ሲሆን፣ የተወለደችው በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ልዩ ስሟ ጨፌ በምትባል መንደር ውስጥ ነው። አትሌት ስለሺ ስኅን ደግሞ 25 ዓመቱ ሲሆን፣ የተወለደው "ሸኖ" በተሰኘችው ከተማ ውስጥ ነው።

 

ከቤጂንጉ ኦሎምፒክ ጋር በተያያዘ ዜና ደግሞ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከትናንት ወዲያ እሁድ ነኀሴ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. በ10 ሺህ ሜትር ርቀት ሲወዳደር የሮጠበት ጫማ ላይ የባለቤቱን የዳናይትን ስም አጽፎ እንደነበር ተሰምቱዋል።

 

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ዳናይት የተጋቡት ኅዳር ወር ላይ 2000 ዓ.ም. እንደነበር ይታወቃል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ