Prof. Merera Gudina

ከአንድ ወር በፊት በብራስልስ የአውሮፓ ፓርላማ ተገኝተው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት ማብራሪያ ሰጥተው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ወዳልታወቀ እስር ቤት የተወሰዱትን ፕ/ር መረራ ጉዲናን በሚመለከት የሚሰጡት መግለጫዎች እየተጣረሱ ነው።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ፓርቲ ዋና ሊቀመንበር ፕ/ር መረራ ጉዲና በቁጥጥር ስር ሲውሉ የመንግስት ባለስልጣናት የየስራቸው ምክኒያት ሀገሪቱ አሸባሪ ብላ የፈረጀቻቸው ድርጂቶች መሪዎች ጋር በመገናኘታቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በወቅቱ ፕሮፌሠሩ ከርበኞች ግንቦት ሰባት የትጥቅ ትግልሊቀመንበር ከሆኑት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንዲሁም በሪዮ ኦሎምፒክ ማራቶን የብር ሜዳሊያ ባለቤት ለሊሳ ፈይሳ ጋር በመሆን በመድረክ መታየታቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ዛሬ የወጣ አንድ መግለቻ እንደሚያሳየው በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዶክተሩ የታሰሩት ከሽብርተኛ ቡድን መሪዎች ጋር በመገናኘታቸው እንዳልሆነ ተገልጿል።

በመሆኑም የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው የተጠረጠሩበት ትክክለኛ ወንጀል ምን እንደሆነ ለማወቅ አዳጋች ሆኗል።

በበርካቶች ዘንድ የተነቀፈው የኢትዮያ ጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ማንኛውም ዜጋ በሽብርተኝነት ከተጠረተረ ሰው ጋር ማውራት፣ መገናኘትና መወያየት ወንጀል እንደሆነ ይደነግጋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ