ለይኩን እሸቱ. Leyikun Eshetu(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከሚኖርበት ሆላንድ ወደ ትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ የገባው ወጣት ለይኩን እሸቱ፤ በፋሲካ በዓል ዋዜማ ስምንት ቦታ በስለት ወግተው የገደሉት ወንጀለኞች እስካሁን አልተያዙም። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ገዳዮቹ ባለጊዜዎች ስለሆኑ ሟች ደመ ከልብ ሆኖ ቀርቷል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የአካባው ነዋሪ ሲናገሩ፣ "ፍጹም፣ ቴዲ እና ባርያው በመባል የሚታወቁ እነዚህ ተጠርጣሪ ነብሰ ገዳዮች፤ በአካባቢው ነዋሪን በእጅጉ ሲያስጨንቁ የኖሩ ናቸው። ይህ ግድያ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከወር በፊትም የንጹህ ዜጋ ዓይን አፍስሰዋል። ፖሊስ ግን አይይዛቸውም።" ብለዋል።

ይህ ሁሉ ሲሆን ፍትህ የሚያስከብር የመንግሥት አካል እና ሕግ አስከባሪ ጉዳዩን ችላ ብሎታል። ከአንዳንዶች እንደሚሰማው ከሆነ ፖሊስ ለወንጀለኞቹ ሽፋን እየሰጣቸው ነው። ከሟች የቀብር ሥነሥርዓት በኋላ ህዝቡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ፖሊስ ድረስ በመሄድ ተጠርጣሪዎቹ በአስቸኳይ እንዲያዙ ቢጠይቅም፤ ፖሊስ ለህዝቡ በጎ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፤ በህዝቡ ላይ ተኩስ በመክፈት ለቀስጠኛው እንዲበተን አድርጓል። ቪድዮውን ይመልከቱ።

የሟች ጓደኛ ዳንኤል ንጉሴም በግድያው በተጠረጠሩት አምስት ግለሰቦች በሳንጃ ተወግቶ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከፍተኛ ቀዶ ጥገና ተደርጎለታል።

ለዚህ አሰቃቂ ግድያ እና አደጋ መነሻ የሆነ ምክንያት እንደሌለ ነው ሰዎች የሚናገሩት። ከሕግ በላይ የሆኑ ባለግዜዎች እና ጉልበተኞች እንዲሁ በማናለብኝነት የፈጸሙት ወንጀል ነው። ሀገሪቱ ሰው ከቤቱ በሰላም ወጥቶ ለመግባት ምንም ዋስትና የሌለበት ሀገር ሆናለች።

ይህ አሰቃቂ ግድያ በሆላንድ የሚኖሩ የለይኩን ወዳጆችን በእጅጉ አስደንግጧል። ከቶውንም "ዲያስፖራ"፣ "ኢንቨስተር" … ወዘተ እየተባለ የሚለፈለፈው ሁሉ ለዲያስፖራው ዋስትና ከማይሰጥ መንግሥት መሆኑም አሁን ግልጽ የሆነ ይመስላል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ