ጫቱን ሲያስገቡ የተያዙት የሦስት ዓመት እስራት ይጥብቃቸዋል
በሕገወጥ መንገድ ከሎንዶን ወደ ስዊድን ሲግባ የተያዘ ጫት Chat, Foto: Scanpix

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. May 9, 2014)፦ 816 ኪሎ ጫት ከሎንዶን በስዊድንዋ የወደብ ከተማ ጉተምበርግ በኩል በመርከብ ተጭኖ ሲገባ አፕሪል ላይ መያዙንና ሁለት ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሜትሮ ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ አስነብቧል።

ባለፈው ዓመት 7 ነጥብ 5 ቶን ጫት ወደ ስዊድን ሲገባ የተያዘ ሲሆን፣ በዚህ በያዝነው 2014 አራት ወራት ውስጥ ብቻ 5 ነጥብ 4 ቶን ጫት ተይዟል።

ስዊድን ጫትን አደንዛዥ ዕፅ ብለው ከፈረጁት ሀገራት ውስጥ አንዷ ነች። በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ሁለቱ ግለሰቦች የ3 ዓመት እስራት ሊቀጡ እንደሚችሉ ሜትሮ አክሎ ዘግቧል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ