Ethiopia Zare (ቅዳሜ ታህሳስ 17 ቀን 2002 ዓ.ም. December 26, 2009)፦ በትግራይ ህወሓትን እየተቀናቀነ ያለው ዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነት ፓርቲ ታህሳስ 11 ቀን በአዲግራት ያደረገው ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የፓርቲው ዋና ፀሐፊ ገለጹ።

 

ፓርቲው በታህሳስ 10 ቀን በእንዳስላሴ የጠራው ስብሰባ በአገዛዙ ካድሬዎች አፈና ምክንያት ስኬታማ ሳይሆን እንደቀረም ለማወቅ ተችሏል።

 

የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አቶ አስራት አብርሃም እንደገለጹት፤ የእንዳስላሴው ስብሰባ ያልተሳካው ያሰቡትን ያህል ተሰብሳቢ ባለመምጣቱ ሲሆን፤ በአዲግራት ግን ካሰቡት በላይ ሰው በመገኘቱ ስብሰባው በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን ገልጸዋል።

 

በእንዳስላሴ 120 ሰው ብቻ ነው የተገኘው ያሉት አቶ አስራት፤ ምክንያቱ ህወሓት ተመሳሳይ ስብሰባ በአመራሮቹ አማካኝነት መምህራንን በመጥራቱና ተሰብሳቢዎቻችንን ወደ አዳራሽ እንዳይገቡ ስላስፈራሩዋቸው ነው ብለዋል። በአዲግራት ከ800 በላይ ተሰብሳቢዎች ተገኝተዋል ተብሏል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ