Ethiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2002 ዓ.ም. September 24, 2009)፦ አሻራ እንዲሰጡ የተጠየቁ የፖሊስ አባላትና አንዳንድ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት አሻራ ለመሥጠት ማንገራገራቸውን አንድ የአሻራ ባለሙያ ገለጹ።

 

በጉለሌ ክፍለ ከተማ የታክስና ግብር ሰብሳቢ ቢሮ የአሻራ አሰባሰብ ባለሙያ እንደገለጡት፤ በሕግ ማስከበር ስራ ላይ የተሠማሩና የኢህአዴግ ሹመት የተሠጣቸው ባለሥልጣናት አሻራ ሥጋት ሆኖባቸዋል ብለዋል።

 

በተለይም ፖሊሶቹ “አሻራን በሥራ ሂደት እናውቀዋለን፣ ለረጅም ጊዜ ሰዎችን አሻራ እንዲሠጡ ስናስገድድ ቆይተናል፤ እኛ ልንታለል አንችልም። አሻራ ሌላ ተልዕኮ የለውም ከወንጀል ተግባር ጋር የተገናኘ ነው” በማለት ሊሰጡ ባለመፈለጋቸው ከፍተኛ ባለሙያዎች መጥተው ሊያስረዷቸው ሞክረዋል። “እናንተ ወንጀልን ለምን ትፈራላችሁ? ሕግ አስከባሪ ሆናችሁ…” የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ፖሊሶች፤ በሥራ ሊያጋጥም በሚችል ስህተት ወህኒ መውረድ አንፈልግም ማለታቸው ተወስቷል።

 

ባለሙያው አያይዘው ፖሊሶቹ ተራ አባላት ብቻ ሳይሆኑ በአዛዥ ደረጃ ላይ ያሉ፥ በኮሌጆች ደረጃ ትምህርት የቀሰሙ እንደሆኑም ገልጸዋል። ካንገራገሩት ሰዎች መካከል ጥቂቶች በአቋማቸው ፀንተው አሻራ ሳይሰጡ ሄደዋል ብለዋል።

 

በአመራር ደረጃ ላይ ያሉ ባለሥልጣናትም“ እኛ ገዥውን መደብ እያገለገልን ለምንድን ነው አሻራ የምንሰጠው” በሚል ጥለው ሄደዋል።

 

የባለሥልጣናቱ ሥጋት ከሙስና ጋር የተያየዘ እንደሆነ የገመቱት እኚህ ባለሙያ እጃቸው ከተነካካ የፓርቲው መጠቀሚያ አሻንጉሊት እንሆናለን የሚል ሥጋት እንዳላቸው አልሸሸጉም። የደሞዝ ግብር አሻራ እስካሁን በጊዜ ገደቡ መሠረት ሊጠናቀቅ እንዳልቻለ ይታወቃል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ