L. Gen. Bacha Debele

ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ መግለጫውን በሰጡበት ወቅት (ፎቶ፣ ከኢቲቪ ስክሪን ሹት)

ሠራዊቱ ማጥቃት እንዳለበት ወስኖ እየሠራበትም ነው ብለዋል

ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 14, 2021)፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጐን እንዲቆም የአገር መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ገለጹ። ጁንታው ትንኮሳውን መቀጠሉንም ሌ/ጄኔራሉ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማምሻውን በሰጡት ተጨማሪ መረጃ፤ ሕዝቡ መገንዘብ አለበት ብለው የገለጹት ደግሞ ወታደራዊ ሥራ በወታደር እንጂ በአክቲቪስቶች የሚከናወን አለመኾኑን ነው።

“ጉዳዩ ውጊያ ነው” ያሉት ሌ/ጄኔራል ባጫ፤ የአገር መከላከያ ሠራዊት በየት ቦታ መቼ ማጥቃት እንዳለበት ተወስኖ እየተሠራበት የሚደረገው ውጊያው ኢትዮጵያን እንደ አገር የማስቀጠል ስለመኾኑን በማስረዳት፤ የወያኔ ኢትዮጵያን የመበተን እቅድ እንደማይሳካ ማሳየት ብቻ ሳይኾን፤ ማረጋገጥም አስፈላጊ ስለኾነ፤ ሁሉንም ኃይላችንን በመጠቀም የት ቦታ፣ መቼ እናጠቃለን የሚለውን ነገር በሚገባ እየተሠራበት መኾኑንም ገልጸዋል።

“እየተዋጋን ያለነው ለኢትዮጵያ ድንበር ነው” በማለት ያከሉት ጄኔራሉ፤ “የእኛ ድንበር መረብ ነው” ብለዋል።

የመረብ ድንበር ድረስ ማንም አጉራ ዘለልና የመንደር ዱርዬ ተነስቶ ኢትዮጵያን ለመበጣጠስ የሚፈልገውን ኃይል፤ የማይቻል መኾኑን ማሳየት እንጂ፤ እንደ መከላከያ ሠራዊት የት ቦታ መቀመጥ እንዳለብን፤ በፊት መቀመጥ ያለበትን ቦታ ስንወስን እዚህ ጋር ነን ብለን ካምንም ጋር ኮምዩኒኬት አላደረግንም፤ አልተነጋገርንምም ብለዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ