የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን በመስቃንና በማረቆ ቁጥር ሁለት ምርጫ ክልል የግል እጩ ተወዳዳሪ ኾነው የተመዘገቡት እንዲፈታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠየቀበት ደብዳቤ

የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን በመስቃንና በማረቆ ቁጥር ሁለት ምርጫ ክልል የግል እጩ ተወዳዳሪ ኾነው የተመዘገቡት እንዲፈታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠየቀበት ደብዳቤ

በኢትዮጵያ ምርጫ ሕግ መሠረት እጩ ተወዳዳሪዎች ምርጫው እስኪያልቅ ድረስ የማይያዙና ሕገወጥ ድርጊት ፈጽመው ከኾነም ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድባቸው የምርጫው ውጤት ከታወቀ በኋላ ነው

ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 15, 2021)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያሰራቸውን ሁለት የግል እጩ ተወዳዳሪዎችን እንዲፈታ ጠየቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በመረጃ ገጹ እንዳሰፈረው፤ በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የታሰሩ ሁለት የግል እጩ ተወዳዳሪዎች እንዲፈቱ የጠየቀው ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር ምርጫ እስኪጠናቀቅ የማይያዙ መኾኑ በሕግ የተደነገገ በመኾኑ ነው።

የክልሉ ፖሊስ እጩዎችን ያሰራቸው ከዚህ በፊት ተጠርጥረውበታል በተባለ የወንጀል ክስ ጉዳይ መኾኑን ቦርዱ የተረዳ ቢኾንም፤ በኢትዮጵያ ምርጫ ሕግ መሠረት እጩ ተወዳዳሪዎች ምርጫው እስኪያልቅ ድረስ የማይያዙና ሕገወጥ ድርጊት ፈጽመው ከኾነም ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድባቸው የምርጫው ውጤት ከታወቀ በኋላ ነው ብሏል።

የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን ይሕንን ተገንዝቦ በመስቃንና በማረቆ ቁጥር ሁለት ምርጫ ክልል የግል እጩ ተወዳዳሪ ኾነው የተመዘገቡት እና አሁን በእስር ላይ ያሉትን ሁለት ግለሰቦች ከእስር እንዲፈታ ቦርዱ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162\2011 አንቀጽ 42 ለምርጫ የተመዘገቡ የእጩዎች ልዩ መብትን በተመለከተ እንደደነገገው፤ ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር ምርጫው እስከሚጠናቀቅ ድረስ በወንጀል ተጠርጥረው አይያዙም ይላል።

በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) እንደተጠቀሰው እጅ ከፍንጅም ባይኾን እጩዎች ሕገወጥ ድርጊት የፈጸሙ እንደኾነ ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው የሚችለው የምርጫው ውጤት በቦርዱ አማካኝነት በይፋ ለሕዝብ ከተገለጸ በኋላ ብቻ ነው። ቦርዱ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የጻፈው ደብዳቤ የሚከተለው ነው። (ኢዛ)

የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን በመስቃንና በማረቆ ቁጥር ሁለት ምርጫ ክልል የግል እጩ ተወዳዳሪ ኾነው የተመዘገቡት እንዲፈታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠየቀበት ደብዳቤ
የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን በመስቃንና በማረቆ ቁጥር ሁለት ምርጫ ክልል የግል እጩ ተወዳዳሪ ኾነው የተመዘገቡት እንዲፈታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠየቀበት ደብዳቤ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ