ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጆ ባይደንና ምክትላቸውን እንኳንም አሸነፋችሁ አሉ
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ (ግራ)፣ ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን (መኻል) እና ቀጣይ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሐሪስ
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው
ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 7, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንትት ጆ ባይደን እና ለምክትላቸው ካማላ ሐሪስ የእንኳን ደስ አላችሁ የሚል የደስታ መግለጫ መልእክት አስተላልፈዋል።
በትዊተር ገጻቸው [“እንኳንም አሸነፋችሁ!”] ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ፤ ኢትዮጵያና አሜሪካ በቅርበት የሚሠሩ ስለመኾኑ ያላቸውን እምነት አስፍረዋል።
ዴሞክራቱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ የዓለማችን አገሮች እንኳንም አሸነፉ፤ እንኳንም ድስ አልዎት እየተባሉ ነው።
ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። (ኢዛ)



