Total coronavirus cases in Ethiopia, August 20, 2020

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ (ሐሙስ ነኀሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም.)

በቫይረሱ ተጠቅተው የሞቱት 620 ደርሰዋል

ኢዛ (ሐሙስ ነኀሴ ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 20, 2020)፦ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ በሚባል ደረጃ እየጨመረ በመምጣት፤ በአንድ ቀን 1,778 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን የሚያመለክት ሪፖርት ዛሬ ተደረገ። ከዚህ ቀደም ከፍተኛውና በአንድ ቀን ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች የተመዘገበው ባለፈው ቅዳሜ ሲሆን፤ ቁጥሩም 1,652 ነበር። በአምስት ቀን ውስጥ በዛሬው ዕለት ያ አኀዝ በ126 ጭማሪ አሳይቷል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 21,456 ሰዎች ላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው፤ 1,778 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የሚያመለክተው የዛሬው (ሐሙስ ነኀሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም.) የጤና ሚኒስቴር መረጃ፤ 20 ሰዎችም በቫይረሱ ተይዘው መሞታቸውንም ጠቅሷል።

የዛሬው ዕለታዊ መረጃ እንደሚያመለክተው በጽኑ የታመሙት ሰዎች ቁጥር 248 ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ከበሽታው ያገገሙት 228 በመኾናቸው ጠቅላላ ከበሽታው ያገገሙትን ቁጥር 13,536 አድርሶታል።

በዛሬው መረጃ መሠረት አጠቃላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 620 ከፍ ብሏል። አጠቃላይ የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 694,093 የደረሰ ሲሆን፤ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ 35,836 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ