ሳሪስ አካባቢ በባቡር አንድ ሰው ገጭቶ ቆሟል
በአዲስ አበባ ያለው በኤሌክትሪክ የሚሠራው የከተማ ውስጥ ባቡር
የገተጨው ግለሰብ በሕይወት መኖር አለመኖሩ አልታወቀም
ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 23, 2020)፦ ሳሪስ አደይ አበባ አካባቢ የከተማ ውስጥ ባቡር አንድ ሰው ላይ ግጭቶ ማድረሱ ተጠቆመ። የተገጨው ግለሰብ በሕይወት መኖር አለመኖሩ አልታወቀም።
ዛሬ መጋቢት 14 ቀን ማምሻውን ደረሰ በተባለ የባቡር አደጋ ከለገሃር ወደ ማሠልጠኛ ይጓዝ ነበር የተባለው ባቡር ሐዲድ ስር የገባውንና አደጋ የደረሰበትን ግለሰብ ለማውጣት ጥረት እየተደረገ መኾኑን በአካባቢው ያሉ የዓይን እማኞች ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ ገልጸዋል።
ባቡሩ ጉዞውን ያቆመ ሲሆን፣ የድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች በአካባቢው ደርሰው የተገጨውን ሰው ለማውጣት እየጣሩ ነው መኾኑን እነኝሁ የዓይን እማኞች ገልጸዋል። ግለሰቡ በሕይወት ይኑር አይኑር እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። (ኢዛ)



