የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 አገሮች በረራ አቆመ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ለ14 ቀኖች በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ ተጣለባቸው
ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 20, 2020)፦ በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት በረራዎቹን እንዲያቋርጥ ተደጋጋሚ ውትወታ ሲደረግበት የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ወደ 30 አገሮች የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ።
ይህንን በብዙዎች ዘንድ ሲጠበቅ የነበረ ውሳኔ፤ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከውጭ ከየትኛውም አገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞችም ለ14 ቀኖች በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ እንደተጣለባቸውም አስታውቀዋል።
እነዚህ ከውጭ የሚመጡ መንገዶች የ14 ቀን የማቆያ ቆይታቸውንም ወጪ ራሳቸው እንዲሸፍኑ ውሳኔ መሠጠቱም ታውቋል። (ኢዛ)



