የኮሮና ቫይረስ ምርመር ላለማድረግ ያመለጠው ግለሰብ ከቫይረሱ ነፃ ኾነ
ወሎ
አምልጦ ደቡብ ወሎ ላይ ነበር የተያዘው
ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 16, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች በማሳየቱ ተጨማሪ ምርመራ ሊደረግለት ሲል፤ አምልጦ ደቡብ ወሎ ላይ የተያዘው ግለሰብ የምርመራ ውጤት ከቫይረሱ ነፃ መኾኑን አመለከተ።
ግለሰቡ በክትትል ደቡብ ወሎ ላይ ተይዞ እንዲመጣና ምርመራውን እንዲካሒድ ከተደረገ በኋላ፤ የተገኘው የላቦራቶሪ ውጤት ነፃ መኾኑን፤ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ግለሰቡ ከሳውዲ ዐረቢያ የመጣ መኾኑን መዘገባችን አይዘነጋም። (ኢዛ)



