ብልጽግና ፓርቲ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገቢ እያሰባሰበ ነው
ብልጽግና ፓርቲ
ገቢ ማሰባሰቢያው ለመጪው ምርጫ 2012 ዝግጅት ነው
ኢዛ (ቅዳሜ መጋቢት ፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 14, 2020)፦ ብልጽግና ፓርቲ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ እያካሔደ ባለው የገቢ ማሰባሰቢያና እውቅና ፕሮግራም ላይ በቢሊዮን የሚቆጠር ድጋፍ ማግኘቱ ተገልጿል። ፓርቲው ለመጪው ምርጫ 2012 እያደረገ ያለው የገቢ ማሰባሰቢያ መኾኑ ይታወቃል።
እስካሁን በተካሔደው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከተለያዩ ኩባንያዎችና ታዋቂ ባለሀብቶች ቃል የተገባና በብልጽግና አካውንት የገባው ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገልጿል። አሁንም የገቢ ማሰባሰቡ ፕሮግራም እየተካሔደ ነው።
በዕለቱ የተደረገውን ድጋፍ ሳይጨምር ቃል ከተገባው ሌላ የተሰባሰበው የገንዘብ መጠን 1.5 ቢሊዮን ብር ነው። (ኢዛ)



