Pick Pick Taxi Ethiopia

ፒክ ፒክ ታክሲ

ሹፌሮቹን ድርጅቱ አባረረ

ኢዛ (ማክሰኞ የካቲት ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 18, 2020)፦ “ፒክ ፒክ” የተሰኘውና ዘመናዊ የታክሲ አገልግሎት ለመሥጠት የተቋቋመው ድርጅት ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት ሲሠጥ የቆየ ቢኾንም፤ የ“ፒክ ፒክ” ታክሲዎች እንዳይንቀሳቀሱ በፍርድ ቤት ታገቱ። የታክሲ ሹፌሮቹም ከሥራ ታገዱ።

እነዚህን ፒክ ፒክ ታክሲዎች እንዳይንቀሳቀሱ በፍርድ ቤት ያሳገደው ለታክሲዎቹ ግዥ 70 በመቶ የሚኾነውን ወጪ ያበደረው ሕብረት ባንክ ሲሆን፤ ብድሩ ባለመከፈሉ ባንኩ በፍርድ ቤት በማሳገዱ ነው።

በዚሁ ምክንያት የፒክ ፒክ ታክሲ ሹፌሮች ከሥራ እንዲታገዱ ኾኗል። ያለምንም ማስጠንቀቂያ የተባረሩት የታክሲ ሹፌሮች፤ በድርጅቱ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም መብታቸው እንዲጠበቅ ጠይቀዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ