በትግራይ ሕግ የማስከበር ዘመቻው መጠናቀቁን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
ቀጣይ ሥራ ክልሉን ማልማትና ወንጀለኞችን ማደን ነው
ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 28, 2020)፦ በትግራይ ክልል ሲካሔድ የቆየው ሕግን የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው እንዳመለከቱት፤ “በትግራይ ክልል ስናካሒድ የነበረው ሕግ የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁና መቆሙን ላሳውቅ እወዳለሁ” በማለት የገለጹ ሲሆን፤ ቀጣዩ ሥራቸው ክልሉን መልሶ መገንባት፤ እንዲሁም ሰብአዊ ድጋፎችን ማድረስ ስለመኾኑም አሳውቀዋል።
ከዚህ ተግባራቸው ጎን ለጎን የፌዴራል ፖሊስ በሕግ የሚፈለጉ ወንጀለኛ የሕወሓት አባላትን በቁጥጥር ሥር የማድረግ ሥራ እንደሚሠራም በዚሁ መልእክታቸው ላይ አስፍረዋል። (ኢዛ)



