የዋልድባ ገዳም ይዞታና የመነኮሳቱ ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ተጠየቀ
ለአቶ መለስ ዜናዊ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር - አዲስ አበባ)
ጉዳዩ፦ ታሪካዊ የዋልድባ ገዳማችን ይዞታና የመነኮሳት ሰብዓዊ መብት እንዲከበርልን ስለመጠየቅ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ታሪክ ማኅበራዊና ሥነ- ጥበብ እድገት ያበረከተችው አስተዋጽዖ ከኢትዮጵያ አልፎ በመላው ዓለም የሚታወቅ እውነታ ነው።
ቤተ ክርስቲያናችን ባላት ታሪክና መንፈሳዊ ሀብት ለበርካታ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ትልቁን ድርሻ የምትይዝ ሲሆን፣ በዚህም መንግሥትንና የተለያዩ ተቋማትን ተጠቃሚ እያደረገች ስትገኝ፤ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶችም በዋነኛነት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥንታዊያን ገዳማት፣ አድባራት እና እንደ ጥምቀት መስቀል /ደመራ/ እና ልደት የመሳሰሉ ታላላቅ በዓላት መንፈሳዊ አከባበርን ለመመልከት እንደሚመጡ ዘወትር የሚመሰክሩት ነው። … (ሙሉውን መግለጫ አስነብበኝ!)



