“…ከአግባብ ውጪ የተገኘን ገንዘብ ወደ ቤት ማስገባትና መጠቀም ለቤተሰብ እርም ነው፣ አይጠቅምም”… በአፍሪካ የበርካታ መሪዎችና የፖለቲካ ሹመኞች መጨረሻ የተበላሸና በአሳፋሪ ታሪክ የተዘጋ የሚሆነው በምግባራቸው ነው።ማንም ከእውነተኛ ፍርድና ቅጣት አያመልጥምና መልካም ስራ በመስራት ለሚመሩት ሕዝብም ሆነ ለራስ መልካም ሰርቶ ማለፍ ያዋጣል።ዕርቅ ፍትህን ሲያካትት እውነተኛ ዕርቅ ይሆናል። ፍትህ የጎደለበት ዕርቅ ግን የሚፈለገውን ውጤት አያመጣምእኛ የምንሰራው ፍትህ ያለበት ዕርቅ እንዲመጣ ነው።ይህን የተናገሩት የዓለም ሉተራን ቤተ ክርስቲያን የአፍሪካ ሚሽን ዳይሬክተር / ቄስ ገመቺስ ደስታ ናቸው።


ላለፉት 20 ዓመታት በገዢነት፣ቀደም ሲል ደግሞ በሽፍትነት ዘመኑ ህወሃትና መሪው አቶ መለስ የሽምግልና ልመና ያልገባበትና ሽማግሌ ያልጎተተበት ወቅት የለም። በአገር ሽማግሌና በዕርቅ ስም ያላምታታበትን ዘመን መቁጠሩ እንደሚቀል የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው። ለድርድር፣ ለዕርቅና ለሰላምሰጥቶ በመቀበል መርህአብረው ተቀምጠው የአቶ መለስን ቅጥፈት ያዩ ከነመለስ ጋር ተቀምጦ መነጋገር እንደማይቻል አረጋግጠዋል። የቀድሞ የህወሃት አመራሮች በዕርቅ ስም ተጭበርብረው እንጂ የዛሬው ውርደት ከቶውንም ሊከሰት እንደማይችል ነግረውናል። በረሃ ዋሻ ውስጥ ተማምለው፣ ከዋሻው ደጅ ላይ ክህደት እንደተፈፀመባቸው አውግተውናል። አሁንም የሚሆነው ይኸው ነው።


ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ለንደን ላይ ባደረጉት ንግግርከመለስ ጋር ለመነጋገር ከመግባታችን በፊትከሰማይ በታች ባለ ነገር ሁሉ ለመደራደር ዝግጁ ነኝበማለት አደራዳሪዎች ፊት ተናገረ። ድርድሩ ሲጀመርና ወሳኝ ጉዳይ ሲነሳፓርቲዬ መፍቀድ አለበትበማለት ሽምጥጥ አድርጎ ካደ። እነዚህ ታዲያ ቁጭ በሉዎች አይደሉም?” ብለዋል። ይህ የሆነው ቅንጅት አጥቂ በነበረበት ወቅት ላይ ነበር።


ህወሃት ለሁለት ተሰንጥቆ ሳለ የአቶ መለስ ቡድን የኤርትራን ወረራና የንፁሃን እልቂት የቀውሱ ማገገሚያ አደረጉት። ስሟን የማይጠሯትን አገርእንታደጋትበማለት በችግራቸው ዙሪያ ወደፊት እንነጋገር ተባለ፣ በሌላ በኩል የትግራይ እናቶችና አባቶችበተሰውት ሰማዕታት ስምብለው ደረት እንዲመቱ ተደረገ። በቆረጣ የሙስና ህግ ተበጀ። በዚሁ ህግ መሰረት ዋና ተቀናቃኞች ተጠለፉ። በዚህ ግርግር ውስጥ ህዝብና አገር የተፈፀመባቸውን ክህደትና በደል ሰሙ። በሰማዕታት ደምና በታጋዮች አፅም መሃላ ተፈፅሞ ዕርቁ በሸፍጥ ተጠናቀቀ።


ህወሃት ጭንቅ ሲገባው ሁሌምከሰማይ በታችበማለት ለድርድር በሩን መክፈትና ጎን ለጎን ደግሞእኔ ከሌለሁ አገር ትፈርሳለች፣ ኢንተርሃምዌ፣ አኬልዳማ. . .” እያለ አስከሬን መጎተት፣ በራሱ ድራማ ቅቤ አንጓች መስሎ ማስለቀስ፣ ሙሾ ማውረድ፣ ማስደንገጥ፣ ማሸበር የተካነበት ማደናገሪያው ነው። አሁን እየሰማን ያለነው የሽብርና የአሸባሪነት ከበሮ ድለቃ የዚሁ የከረመ ወጉ ነውና የስርዓቱን መናድ ከማሳየት የዘለለ ትርጉም የለውም።


ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት ውድቀት ለመላቀቅ ቀናነትና እርቅን የምትሻበት ወቅት ላይ ትገኛለች። ከማንም በላይ ህወሃት/ኢህአዴግ፣ ይህን እርቅ አጥብቆ ይፈልጋል። የዛሬ ሃያ ዓመት ኦነግን ልደራደርህ ሲለው የበደኖን ስዕል እያሳየ ነበር። ሻዕብያን ልደራደርህ ሲለው የሃይደር ህጻናትን ጭፍጨፋ እያሳየ ነበር። ኢህአፓን ሲማፀን የቀይ ሽብር ሰለባዎችን እያቀረበ ነበር። ኦብነግን እንታረቅ ሲለው የሺላቦን እልቂት እያሳየ ነበር።ቅንጅቶችን እንስማማ ሲል የሩዋንዳን እልቂት እያቀነባበረ ነበር። ዛሬም ይኸው የኖረ ድራማ መደገሙና የሰላም ደቀ መዝሙር ነኝ እያለ ከፍርድ ቤት እስከ ቤተመቅደስ የሚያላዝነው የለመደውን የማገገሚያ እርቅ ለማቀነባበር ነው።


ስለዚህ ምን ይሁን? እንደ ከዚህ ቀደሙ ስህተት እንዳይፈፀም መጠንቀቁ ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ለማለት ነው። ህዝብ ሽምግልናውን እኔ እሰጣለሁ ቢል እንኳን እንዴትና እነማን ያከናውኑታል? ማን ሃላፊነቱን በታማኝነት ተረክቦ የህዝብን ዳኝነት ይቀበላል የሚለው አሳሳቢና ምዕራባዊያኖቹ የሚጠይቁት ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ከወዲሁ መስራት ግድ ይላል።


ህወሃት/ኢህአዴግ በእንጥፍጣፊ ዘመኑ ላይ ለመኖሩ በቂ ማስረጃዎችና ምልክቶች እየታዩ ነው። ህዝብ መሮታል፣ አገር ተርቧል፣ ድህነት ፈሩን ለቋል፣ ኢኮኖሚው ሞቷል፣ ሁለት ዓይነት ዜጎች ተፈጥረዋል፣ ዝርፊያውና አፈናው አይሏል፣ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ መከፋፈል ተፈጥሯል፣ የሚኮበልሉ በዝተዋል፣ ከተሰላዩ ቁጥር በላይ ሰላዩ ገኗል፣ የፍትህ ያለህ የሚሉት ቁጥራቸው አይታወቅም፣ የተፈናቃዮች እምባ ወደ ደም ተቀይሯል፣ቤተክህነትና የእምነት ደጆች ረክሰዋል፣ ባንዳዎች ሽሽት መርጠዋል፣ ሃብት የሰበሰቡ የሚበሉበትን ነፃ መሬት እየተመኙ ነው፣ ስቃይ፣ ግርፋት፣ መደፈር፣ ግድያ ተባብሷል፤ ዳቦ እንኳን መብላት ዘበት ሆኗል፣ ነጋዴው አትነግድ ተብሏል፣ ታላላቅ የህወሃት ኢምፓየሮች የአገራችንን ሃብት በመሰብሰብ ለጠቅላይ እየተጫወቱ ነው . . .ትከሳቱ የሚገነፍልበት የመጨረሻው ደረጃ ደርሷል።ከዚህ በላይ ምን የሚቀር ነገር አለ?


ህወሃት/ኢህአዴግ ገና ስልጣን ሲይዝ እንደሚበተን ስለተረዳእኔ ከሌለሁበማለት የረጨው የዘርና የመከፋፈል መርዝ በመጨረሻዋ ሰዓት ሊያስከትለው የሚችለውን ግርግር ከወዲሁ የሚያመክን ዘመቻ መጀመር አለበት። ከጅምላ አስተሳሰብ በራቀ መሰራት ያለበት ጉዳይ ስለሆነ ህወሃት/ኢህአዴግ ነገ ትን ቢለውና የጨው አምድ ቢያደርጉት መራወጥ ሳይኖር አገር አስክኖ ለመምራት ዝግጅት መጀመር አለበት። በሌላ በኩል በሽግግር ወቅት እንደተፈጸመው አይነት ሸፍጥና ማጭበርበር እንዳይፈፀም፣ አደራዳሪ የሚባሉ ወገኖችም 1997 የፈፀሙትን ተግባር እንዳይደግሙ፣ መደራደሪያው እርቅ ከፍትህ ጋር ሆኖ መጠናቀቅ እንዳለበት የሚያመለክት መሆን አለበትና እዚህ ላይም ሊተኮር ይገባል። እንዲያውም ይህ በተቋም ደረጃ በጥናት መከናወን እንዳለበት የጋራ ንቅናቄያችን ያምናል፡፡


ፍትህና እርቅ እንዴት ይዋሃዳሉ? በህዝብ ዘንድ፣ በሃይማኖት ተቋማትና በወንድማማች መካከል ሊኖር ስለሚገባው የስነ ልቦና ዝግጅት ከተለያዩ ተሞክሮዎች ጋር በማነጻጸር መላ ሊባልለት የሚገባ አብይ ጉዳይ ይሆናል። ዛሬ ህዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ለውጥ ለማድረግም ጫፍ ላይ ነው። ግን ሁሉንም ወገን በንቃት ይከታተላል። እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ትግል መልሶ አረምና ተባይ እንዳይሆን ትግሉ በተለያየ ምዕራፍ መጠናከር አለበት!!


ቄስ ገመቺስ እንዳሉትና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በተደጋጋሚ እንደሚያስታውቀው እርቅ፣ ፍትህና ሰላም እውን ይሆን ዘንድ ሁሉም ወገኖች ድምፃቸውን ያሰሙ፡፡ ከፍትሕ ጋር የተቀናበረ ዕርቅ እንዲሁም ተጠያቂነትንና ግልጽነትን ያካተተ ተግባራዊ ዕቅድ በይፋ ተግባራዊ የሚሆንበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግን በማስወገዱ ብቻ ሳይሆን በታማኝነት ከህዝብ ጊዜያዊ ሃላፊነት በመውሰድ ህዝብ የፈለገውን እዲሰይም መንገዱን የሚጠርጉ ወገኖች ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ይዘጋጁ፣ ይተባበሩ።


አሸናፊነትንና በማሸነፍ እርከን ላይ ስለመሆን ለምታውቁና ህወሃት/ኢህአዴግ እንደ ጨረሰ ለተረዳችሁ በሙሉ፤ ስርዓቱ ራሱን የሚከላከልበት ህጋዊ ሽፋንና ማደናገሪያ እንደ ተሟጠጠበት ለገባችሁ፤ የስድብና የርግማኑ ኮሮጆ ተራግፎአሸባሪበሚለው ማህተም እንደተዘጋ ለተገለጠላችሁ፤ እንደ ፖለቲከኛ የጊዜውን ሙቀት ማንበብ ለቻላችሁ፤ ድርጅትና መሪ ሲያረጁ የሚያሳዩትን ምልክቶች ለምታውቁ፤ ህዝብ ከድቶት ቀፎ የሆነመንግስትለታያችሁ፤የተነጠለ መሪና የተገለለ ተከታይ ያለው ድርጅት ቅዠት ለሚሰማችሁ፣የአዲስ ምዕራፍ ወጋገኑ ለታያችሁ ሁሉ፣አሸናፊ የምትሆኑበት ማማ ላይ በመሆናችሁ ቀጣዩን ስራ ከወዲሁ ጀምሩ!!ጆሮ ያለው ይስማ!!


ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ

________________________

ለዚህ ደብዳቤ ምላሽም ሆነ ለተጨማሪ መረጃ ዋና ዳይሬክተሩን ለአቶ ኦባንግ ሜቶ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.) በመጻፍ ወይም ድረገጻችንን (www.solidaritymovement.org) በመጎብኘት ለመረዳት ይችላሉ።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ